የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት ለኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ክትባት ድጋፍ አደርጉ!

  • Time to read less than 1 minute
EU

ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ክትባት ድጋፍ ከአውሮፓ ህብረት አገራት ተረከበች። 


ድጋፍ ያደረጉ አገራት ሰድስት ሲሆኑ እነሱም ፈርንሳይ (6746 400)፣ ፊላንድ(1699200) ዴንማርክ (1560000)፣ ግሪክ (1346400) ጣልያን (1264110 ) ስዊድን (480690) ዶዝሰ በአጠቃላይ (13 096 800 ዶዝስ) የኮቪድ-19 ክትባት ድጋፍ ማግኘቷ ታውቀዋል። 


በርክክብ ስነስርኣቱ የአገራቱ አምባሳደሮች፣ የኢምባሲ ተወካዮች፣ የዩኒሴፍ ተጠሪዎች የተገኙት ሲሆን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ 
በመድረኩ ላይ ዶክተር ሊያ እንዳሉት የተደረገው ድጋፍ የክትባት አቅርቦትን እንደሚያሳድግ ገልጸው ይህም ለበሽታው መግታትና መከላከል ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ተናግረዋል። 


በአለም አቀፍ ደረጃ የሚደረገውን ክትባቱን ተደራሽ  የማድረግ ስራ ለበሽታው ስርጭትን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለውን ጥረትና ቁርጠኝነት ያመለክታል ብለዋል።
በአገሪቱ ክትባቱን መስጠት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ  መሆኑ ሚኒስትሯ የገለፁ ሲሆን ክትባቱ በአገሪቱ በሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ተቋማት ባሉ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችም አማካኝነት ለህብረተሰቡ ተደራሽ እየተደረገ መሆኑ አስረድተዋል። 


በዚህ ሂደት በህብረተሰቡ ውስጥ ያለው የተሳሳተ ግንዛበቤ፣ የክትባቱ የጎንዮሽ ጉዳት ያደርሳል የሚል ፍርሃት መኖሩ በተግዳሮት ያነሱ ሲሆን ለዚህም የሚድያ አማራጮችን በመጠቀም መልእክቶች ተቀርጾ ግንዛቤ የማሳደግ ስራ እየተሰራ መሆኑ አስረድተዋል።


በመጨረሻም ሚኒስትሯ ለተደገው ድጋፍ ያላቸውን አድናቆትና ምስጋና አቀርበዋል።


 በአጠቃላይ ከዚህ ቀደም ከጀርመንና ፓርቹጋል መንግስታት የተገኘውን ሲጨምር ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት አገራት  24,000,000 ዶዝ የኮቪድ 19 ክትባት ድጋፍ አግኝታለች።