ጥራት ያለውን የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ባለድርሻ አካላት አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ ተጠየቀ

  • Time to read less than 1 minute
universal health coverage day

ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ቀን /INTERNATIONAL UNIVERSAL HEALTH COVERAGE COMMEMORATION DAY/ “የጤና ኢንቨስትመንት ለሁሉም" /INVEST IN HEALTH SYSTEMS FOR ALL/ በሚል መሪ ቃል በዓለም ዓቀፍ ደረጃ እየተከበረ ነው፡፡ 


ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ቀን ሲከበር አጋር አካላት አጋርነታቸውን በመቀጠል በጦርነት የወደሙ ጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋምና ለአገልግሎት ብቁ ለማድረግ እንዲሰሩ ጠይቀዋል፡፡


በተጨማሪም ሁሉን አቀፋዊ የጤና አገልግሎትን ማረጋገጥ ለጤና ብቻ ሳይሆን ድህነትን ለመቀነስ፣ ስርዓተ ምግብን በማስተካከል ልጆች ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ ለማድረግ እንዲሁም ሰላምና ማህበረሰባዊ መረጋጋት እንዲኖር ለማድረግ እንደሚያግዝ ገልፀው የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ  ማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህንና ማህበራዊ ጤና ኢንሹራንስን ማስፋፋትና ሀገር በቀል የገንዘብ ማግኛ ዘዴዎችን ማጠናከር እንዲሁም የተለያዩ ኢኖቬንሽኖችን መጠቀም እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ 


በዓለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ዶ/ር ቦሪማ ሀማ ሳምቦ በበኩላቸው ኮቪድ 19  በጤና ፋይናንሲንግ ላይ ያመጣው ተፅዕኖ ከፍተኛ መሆኑን መረጃዎች እንደሚያሳዩ ገልፀው በኢትዮጵያ ደግሞ  ከኮቪድ 19 በተጨማሪ በሃገሪቱ ያለው የፀጥታ ችግር የጤና አገልግሎቱን እያወከ የሚገኝ በመሆኑ አገልግሎቱን ለማስቀጠል ሁላችንም ባለድርሻ አካላት በትብብር ልንሰራ ይገባል ብለዋል፡፡  


የዓለም አቀፍ ሁለንተናዊ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ቀን የተባበሩት መንግስታት አለም አቀፍ የጤና ሽፋን /universal health coverage /ለአለም እድገት አስፈላጊ እንደሆነ የደነገገበትን ቀን በማስታወስ ባለድርሻ አካላት የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩበት ታልሞ የተጀመረ ነው፡፡


ኢትዮጵያም በዚህ አመት ሁለንተናዊ የጤና ሽፋንን ለማረጋገጥ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና አጠባበቅ አስፈላጊነትን በመደገፍ በመንግስትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የሚወሰዱ እርምጃዎችን በማበረታታት ታከብራለች፡፡