በጅግጅጋ ከተማ የተካሄደው 23ኛው የጤና ዘርፍ ጉባኤ የ2014 ዓ.ም ዕቅድን በጋራ ለማሳካት የሚያስችል የቃል ኪዳን ስምምነት ከክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች ጋር በመፈራረም ተጠናቋል

  • Time to read less than 1 minute
final

"ምላሽ ሰጪ የጤና ስርዓት በአዲስ ምዕራፍ " በሚል መሪ ቃል ለሶስት ቀናት በጅግጅጋ ከተማ ሲከናወን የቆየው 23ኛው የጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ጉባዔ ተጠናቋል።


በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ከዘጠኝ የክልልና ሁለት የከተማ መስተዳድር የጤና ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ባደረጉት ስምምነት መሠረት በበጀት ዓመቱ የተቀመጡ ዕቅዶችን በጋራ ለማሳካት የሚያስችሉ ግብዓቶችን በማሟላትና የተቀናጀ ርብርብ በማድረግ ለህብረተሰቡ ተገቢውንና ጥራት ያለውን የጤና አገልግሎትፍትሃዊና ተገልጋይ ተኮር በሆነ መልኩ ለማቅረብ በስምምነት ፊርማቸው በጋራ ቃል ገብተዋል።


ጉባዔውን በንግግር የዘጉት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ጉባኤው በተሳካ ሁኔታ እንዲከናወን ያደረጉትን አጋር አከላት እና በተለይም የሶማሌ ክልልን ካመሰገኑ በኋላ ሁላችንም በያለንበት ለህብረተሰቡ ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ለማዳረስ ተግተን መስራት ይገባናል ብለዋል።


ጉባዔተኞቹ በቀጣይ 24ኛውን ጉባዔ የአፋር ክልል እንዲያዘጋጅ በምረጥና በሰመራ ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘው አጠናቀዋል።