በጂግጂጋ ዩኒሸርሲቲ ሼህ ሀሰን የቦሬ ሪፈራል ሆሰፒታል የሚገኘው የኩላሊት እጥበት ማእከል እና የጂግጂጋ የደምና ቲሹ ባንክ በዛሬው እለት በጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ተጎብኝቷል

  • Time to read less than 1 minute
visit

የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ አመራሮች ከክልሉ የጤና ቢሮ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በሆስፒታሉ የሚገኙ የMRI ክፍልን፣ የኩላሊት እጥበት ህክምና ማእከልን፣ የደምና ቲሹ ባንክን የጎበኙ ሲሆን በተለይ የከተማዋ ህብረተሰብና ባለሀብቶችን በማሳተፍ የተቋቋመው የኩላሊት እጥበት ህክምና ማእከል አገልግሎት አሰጣጥ ተዘዋዉረው ተመልክተዋል።


የኩላሊት እጥበት ህክምና ማእከሉ ከሱማሌ ና ከአካባቢው ለሚመጡ ተካሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ አገልግሎት ተደራሸ እያደረገ እንደሆነ በጉብኝቱ ተገልጿል። በዚህም በ2013 ዓ.ም ለ724 ታካሚዎች አገልግሎቱን መስጠት  እንደተቻለ ተገልጿል።


በተለይ የጂግጂጋ የደምና ቲሹ ባንክ የመረጃ ስርአቱን ዲጂታላይዝ የማድረግ ስራን ዶ/ር ሊያ ታደሰ በጉኝቱ ወቅት በይፋ ያሰጀመሩ ሲሆን የምርመራ ሂደቱን በአዉቶሜሸን በመታገዝ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተመልክተዋል። 


ይህም ደሙ ከተሠበሰበ በኋላ የሚደረገው  ምርመራ ፈጣንና ጥራቱን  የጠበቀ እንዲሆን የሚያደርግ መሆኑ ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
1993 የተመሠረተው የደም ባንኩ ለመጀመሪያ  ጊዜ በ 2013 ዓ.ም 9391 የደም ከረጢት ከበጎ ፈቃደኞች    በመሠብሠብ በአገሪቱ 3ኛ ደረጃ  የያዘ  የደም ባንክ  መሆኑን የሶማሌ ክልል ደም ባንከ ዳይሬክተር አቶ ዘያድ ኑር ገልጸዋል። 


ቀድሞ 90 ናሙና ብቻ በቀን ይሰራ የነበረውን ማሸን በአውቶሜሽን በመተካት በአንድ ጊዜ እስከ 200 ናሙና መመርመር የሚያስችል ፈጣንና አስተማማኝነት ያለው ስራ መስራት እንደተቻለ ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።