HPCAL Announcements

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ

የጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Medicine, Nursing, Health Officer, Anesthesia, Pharmacy, Medical Laboratory Technology, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatrics Nursing እና Emergency & Critical Care Nursing ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ለተመዘገባችሁ የጤና ባለሙያዎች በሙሉ

1.    ፈተናው በግንቦት 15 እና 16/2016 ዓ.ም በኮምፒውተር የሚሰጥ ሲሆን የፈተናው ፕሮግራም እንደሚከተለው ይሆናል፡-

  • Pharmacy, Public Health, Midwifery, Medical Laboratory Science……………………….15/09/2016 ዓ.ም
  • Nursing, Medicine, Dental Medicine, Paediatric Nursing, Psychiatric Nursing, Emergency & Critical Care Nursing, Medical Radiology Technology, Anaesthesia and Environmental Health ----------------------------------------------------------------------16/09/2016 ዓ.ም

2.    ሁሉም ተመዛኞች በግንቦት 14/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ በ 3፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ (orientation) መከታተል፣ የኮምፒውተር ቅድመ ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን መስራት፤ ወደ ፈተና የሚያስገባውን Username and Password ማወቅ፣ የመፈተኛ ክፍላችሁን መለየት ይኖርባችኋል።

3.    በፈተናው ዕለት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ህጋዊ መታወቂያ)፣ የፈተና መስሪያ ግብዓቶች (እርሳስ፣ ላጲስ፣ መቅረጫ) እና ስትመዘገቡ ሲስተሙ የሰጣችሁን ስሊኘ ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፣


4.    ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች ውጪ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎች እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ መግባት አይፈቀድም፣

5.    በፈተናው ወቅት ተመዛኞች በሁለቱም ክፍለ ጊዜ (ጠዋት እና ከሰዓት በኋላ) አቴንዳንስ ላይ በአግባቡ መፈረም ይኖርባቸዋል፣


6.    የመፈተኛ ጣቢያ ኦንላይን በመረጣችሁት መሰረት ስም ዝርዝራችሁን ከዚህ በታች ያለውን ሊንኩን በመጫን መመልከት ይኖርባችኃል::(Exam Center)

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118275936 መደወል እንዲሁም በ moh.gov.et ላይ EHPLE የሚለው ውስጥ በመግባት ማግኘት ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ፤

  • በምዝገባ ወቅት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሶሻል ሳይንስ ካምፓስ የተመዘገባችሁ ፈተናው ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አምስት ኪሎ የቴክኖሎጂ ካምፓስ የተዛወረ እንዲሁም ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ፔዳ ካምፓስ የተመዘገባችሁ ፈተናው ወደ ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ፖሊ ካምፓስ መዛወሩን እናሳውቃለን
  • ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲመጣ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No)፤ የQR CODE እንዲሁም የተመዘገበበትን ተቋም(Exam Center) የያዘ ወረቀት /ስሊፕ/ print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡