ጳጉሜ 1 የበጎ ፈቃደኝነት ቀን አስመልክቶ የጤና ሚኒስቴር፣  የትምህርት ሚኒስቴር እና የስራና ክህሎት ሚኒስቴር በጋራ የሚያዘግጁት የሙሉ ቀን መርሃ ግብር በሚኒሊክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ እና የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት በተለያዩ ዝግጅቶች ተጀምሯል።

  • Time to read less than 1 minute
Dr. Lia Tadesse

ዛሬ ጳጉሜ 1 የበጎ ፈቃደኝነት ቀን በማስመልከት በአራዳ ክፍለ ከተማ በሚኒሊክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ እና የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት ተቋማትን ፅዱና ውብ በማድረግ እንደዚሁም የተተከሉ ችግኞችን በማረም ፣ በመኮትኮት እና በመንከባከብ መርሃ ግብር  ተጀምሯል።

በማስጀመሪያ መርሀ ግብሩ ላይ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌስር ብርሃኑ ነጋ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

መርሀ ግብሩ ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት ተቋማት ለተማሪዎች ምቹ ፣ ፅዱ፣ ውብና ማራኪ እንዲሁም ሳቢ እንዲሆኑ እና ለመማር ማስተማሩ ሂደት ጉልህ ሚና እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚያስችል ነው።

ጳጉሜ 1 የበጎ ፈቃደኝነት ቀን በተለያዩ መርሀ ግብሮች የሚቀጥል ይሆናል።