የፋይናንስ እና ግዥ ዳይሬክቶሬት

finance

ከመንግስትም ሆነ ከልማት አጋሮች የተገኙ የገንዘብ ሀብቶች ተገቢ አጠቃቀምን ማረጋገጥ!

 

የዳይሬክቶሬቱ ዓላማ

የፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት ዓላማ ከመንግስትም ሆነ ከልማት አጋሮች የተገኙ የፋይናንስ ሀብቶች ተገቢ አጠቃቀምን ከማረጋገጥ በተጨማሪ የሚኒስቴሩ የገንዘብ ገቢና ወጪዎች በሀገሪቱ የፋይናንስ ሕጎችና መመሪያዎች መሠረት መከናወናቸውን እንዲሁም የጤና ልማት አጋሮች መስፈርቶችን ማክበራቸውን ማረጋገጥ ነው። በተጨማሪም የእርዳታ ፈንድ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ለታለመበት ዓላማ መዋሉን ማረጋገጥ እንዲሁም በተሰጠው ጊዜ ውስጥ ሪፖርት ማድረግ፣ ለጤናው ዘርፍ ስኬት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ዕቃዎችና አገልግሎቶችን አቅርቦትና አስተዳደርን ማመቻቸት የዳይሬክቶሬቱ ዓላማ ነው።

 

የዳይሬክቶሬቱ አደረጃጀት

የገንዘብና ግዥ ዳይሬክቶሬት ተጠሪነቱ ለሚኒስትር ዴኤታ ኦፕሬሽን ክንፍ ነው። በአሁኑ ጊዜ ዳይሬክቶሬቱ በስሩ ስድስት የጉዳይ ቡድኖች አሉት። እነዚህም የመንግስት አካውንት ጉዳይ ቡድን ፣ የግራንት ፋይናንስ ጉዳይ ቡድን ፣ የግራንት ማኔጅመንት የጉዳይ ቡድን ፣ የግዥ ጉዳይ ቡድን ፣ የንብረት አስተዳደር ጉዳይ ቡድን እና የተቀናጀ የፋይናንስ አስተዳደር መረጃ (IFMIS) የጉዳይ ቡድን ናቸው። በዳይሬክቶሬቱ ስር ያሉት አጠቃላይ ሠራተኞች ቁጥር 73 (45 ወንድ እና 28 ሴት) ነው።

 

የመንግስት አካውንት ጉዳይ ቡድን

  • ለካፒታል ፣ ለደመወዝ እና ለአሠራር እንቅስቃሴዎች ከ MOFED በጊዜው በጀት መጠየቅ
  • ለተለያዩ ገቢዎች ቫውቸሮችን መቀበሉን ማሳወቅና በትክክል መመዘገቡን ማረጋገጥ
  • በመንግስት ከተመደበው በጀት ጋር በሚስማማ መልኩ ክፍያ መፈፀም
  • ለኦዲተሮች ጥያቄዎች ወቅታዊና ተገቢ ምላሽ መስጠት
  • በግምጃ ቤት በጀቶች ደረሰኝና አጠቃቀም ላይ ሪፖርቶችን ማዘጋጀትና ማቅረብ
  • የአካውንት ደብተሮችን በወቅቱ መዝጋትና ለውስጥና ለውጭ ኦዲተሮች ለግምገማ ማቅረብ እንዲሁም የኦዲት ግኝቶች ላይ የማስተካከያ እርምጃዎችን መውሰድ
  • ለሚኒስቴሩ ማንኛውም አገልግሎቶች ፣ ግዢዎች ፣ ደሞዝ ፣ አበል እና ሌሎች የፋይናንስ ግዴታዎች ክፍያዎችን መፈፀም

 

የግራንት ፋይናንስ ጉዳይ ቡድን

  • ከልማት አጋሮች የተገኘ ገንዘብ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ማረጋገጥ
  • ሪፖርቶችን በየጊዜው ለባለድርሻ አካላትና ለአስተዳደሩ ማቅረብ
  • ለአገልግሎታቸው ክፍያ ያልተፈፀመና የሚከፈልባቸው አካውንቶችን ተከታትሎ መክፈል
  • የፋይናንስ ስቴትመንቶችን ትክክለኛነት ማረጋገጥና መቆጣጠር
  • ከተለያዩ የልማት አጋሮች የተገኙ ሀብቶችን መዝገቦች በትክክል ማቆየት
  • በክልል ጤና ቢሮዎች እና በሌሎች አስፈፃሚ ኤጀንሲዎች ላይ የቁጥጥር ተግባራትን መፈፀም
  • በውጫዊ እና ውስጣዊ ኦዲተሮች የሚፈፀሙ ሁሉንም የኦዲት እንቅስቃሴዎች ማመቻቸት
  • በኦዲተሮች አስተያየት ላይ በመመርኮዝ የማስተካከያ እርምጃዎችን መውሰድ
  • ከመተግበሪያ አጋሮች ጋር የአካዉንት ስቴትመንት ልውውጥ ማድረግና መዝገቡን በየጊዜው ማደስ
  • የግራንት ፋይናንስ አስተዳደር ክፍተቶችን በየደረጃው መለየትና ይህን ለመሻገር ዕቅድ ማውጣት

 

የግዥ ጉዳይ ቡድን

  • ለሸቀጦችና አገልግሎት አቅርቦቶች ኮንትራቶችን ለማዘጋጀት ተጫራቾችን መገምገም
  • የግዢ አፈፃፀምን በተመለከተ ለክልል ጤና ቢሮዎች እና ለፌዴራል ሆስፒታሎች ድጋፍ መስጠት
  • በሚኒስቴሩ የግብዓት መስፈርቶች መሠረት የግዥ ዕቅዶችን ማዘጋጀት
  • ከዳይሬክቶሬቶች እና ከቢሮዎች በቀረበ ጥያቄ መሠረት በአገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የእቃዎችን እና አገልግሎቶችን ግዥ ማከናወን
  • በግዥ ሂደቶች ላይ የመንግስት ፖሊሲንና የአሠራር ሂደቶችን በማክበር ግልፅነትን እና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ
  • ዓመታዊ የግዥ ፍላጎቶችን መጠየቅ፣ ከሚኒስቴሩ ጽ / ቤቶችና ዳይሬክቶሬቶች መሰብሰብ፣ እና የተጠናከረ የግዥ ዕቅድ በማውጣት ግዥውን በግልፅ ጨረታ ማከናወን
  • በውጪ ወኪሎች አማካይነት የሚከናወኑትን ሁሉንም ግዥዎች የፌዴራል መንግስት እና የንብረት ማስወገድ አገልግሎትና የህዝብ ግዥን ጨምሮ በቅርብ መከታተል
  • የውጭና የውስጥ ኦዲተሮች በግዥ ላይ የሚያረጉትን ሁሉንም የኦዲት እንቅስቃሴዎች ማመቻቸት
  • በኦዲተሮች አስተያየት ላይ በመመርኮዝ የማስተካከያ እርምጃዎችን መውሰድ እና በግዥ ላይ መደበኛና ወቅታዊ ሪፖርት ማቅረብ

 

የግራንት አስተዳደር

  • በተስማሙበት ዝርዝር የአፈፃፀም ዕቅድ  መሰረት ከልማት አጋሮች ፈንድ መጠየቅና ለትግበራ በወቅቱ ማግኘት
  • ከፈፃሚ አጋሮች ጋር የመግባቢያ ስምምነት(MOU) መፈራረምን ማመቻቸት
  • ፈንዶች ለፈፃሚ አጋሮች በወቅቱ መዘዋወራቸውን ማረጋገጥ
  • ንዑስ ተቀባዮችን የመምረጥ ሂደት ማመቻቸትና ከንዑስ ተቀባዮች ጋር የተፈፀሙ ውሎችን ማስተዳደር
  • ለባለድርሻ አካላት ከመሰጠቱ በፊት የአጠቃላይ እና የፋይናንስ ሪፖርቶችን ማመሳከር
  • የግራንት ሪፖርትን ለአስተዳደር እና ለባለድርሻ አካላት በወቅቱ ማቅረብ
  • ከልማት አጋሮች ጋር በመመካከር ቀደም ሲል የተስማሙባቸውን እንቅስቃሴዎች እንደገና ፕሮግራም ማድረግ ወይም ማዘዋወር
  • በተስማሙበት የጊዜ ሠንጠረዥ ውስጥ ፕሮጀክቶች መጠናቀቃቸውን ማረጋገጥ
  • ፕሮጀክቶች በሰዓቱ መዘጋታቸውን ማረጋገጥ
  • የግራንት ፈንዶችን ኦዲት መከታተልና በኦዲት ግኝቶች ላይ እርምጃዎችን መውሰድ

 

የንብረት አስተዳደር ጉዳይ ቡድን

  • በግዥ ፣ በስጦታ ወይም በእርዳታ የተገኙ ንብረቶችን ሁሉ መቀበል፣ ማደራጀት፣ ማቆየትና ቁጥጥሩን ማስተዳደር
  • በትክክለኛ ፈቃድ መሰረት ንብረቶችን መስጠትና ማሰራጨት
  • በሚመለከታቸው ህጎችና ሂደቶች መሠረት የፍጆታ ቁሳቁሶችንና ቋሚ ንብረትን መለያየት ማካሄድ
  • በሚኒስቴሩ ቁጥጥር ስር ያሉ ሁሉም ንብረቶች ዓመታዊ የክምችት ቁጥጥር ማካሄድ
  • የንብረት ሪፖርቶችን በመደበኛነት ለአስተዳደር ማቅረብ
  • የሚኒስቴሩ ዓመታዊ የአቅርቦት መስፈርቶች ለግዥ ጉዳይ ቡድን ማቅረብ
  • በመንግስት የማስወገድ ፖሊሲ ላይ በመመስረት የእቃዎችን ማስወገድ ማካሄድ
  • በንብረት አስተዳደር ላይ አማራጭ አቅጣጫን ማቅረብና ሲፀድቅ መተግበር

 

የ IFMIS ጉዳይ ቡድን

  • የሚኒስቴሩ የፋይናንስ አስተዳደርና የውስጥ ቁጥጥር ዘመናዊና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው መሆኑን ማረጋገጥ
  • የሂሳብ ስራዎችን የሚያጣምር የተቀናጀ የፋይናንስ ስርዓት ማቋቋም
  • ስለ IFMIS ጥቅም በጤና ተቋማት ሁሉም ደረጃዎች ውስጥ ማስተዋወቅ እና ማስገብየት
  • ለሁሉም የ IFMIS ተጠቃሚዎች ስልጠና እና ቀጣይ ድጋፍ መስጠት
  • በብሔራዊ የጤና ተቋማት ውስጥ የሥራ ሂደቶችን መደበኛ ማድረግ
  • በብሔራዊ የጤና ተቋማት ውስጥ ከተመሳሳይ የመረጃ ምንጭ ሰፊ ጥራት ያለው የሪፖርት ማቅረቢያ መገልገያዎች ያለው አንድ ስርዓት ማንቃት
  • የአሁኑን የበጀት ስርዓት ወደ ውጤት ላይ የተመሰረት የበጀት ዘዴዎች  ለማዘጋጀት መድረክን መጥረግ