79ኛዉ የዓለም ጤና ጉባኤ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ እየተካሄደ ይገኛል

  • Time to read less than 1 minute
WHA79


በጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የተመራዉ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በጄኔቫ እየተካሄደ በለዉ 79ኛዉ የዓለም ጤና ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።


በጉባኤዉ ላይ ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በቅርቡ ይፋ የሆነዉ የህብረተሰብ ጤና ዳሰሳ ጥናት ግኝት መሰረት ኢትዮጵያ የእናቶችና ህጻናት ሞትን በመቀነስ ረገድ አመርቂ ዉጤት ማስመዝገቧን በመግለጽ በቀጣይም አለም አቀፍ የጤና ተደራሽነትን በማረጋገጥ ለመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ ጠንካራ የጤና ስርዓት እንዲፈጠር በትጋት እንደሚሰራ አጽንኦት በመስጠት ተናግረዋል። 


በመላዉ ህብረተሰብ ተሳትፎና የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ቅንጅት እንዲሁም የጤና ባለሙያዉን  ተነሳሽነትና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የእናቶችና ህጸናት ጤናን በቀጣይነት ማሻሻል፣ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን መከላከልና መቆጣጠር፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ጥራት ያለዉ የጤና አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆን በትኩረት እንደሚሰራ የገለጹት ሚኒስትሯ ኢትዮጵያ ቀጣይነት ያለዉ የጤና ልማት ግቦችን ለማሳካት ከዓለም ጤና ድርጅት፣ ከአፍርካ ህብረት፣ ከሀገራት፣ ከሀገር በቀልና አለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች እንዲሁም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል።

#WHA79