የቻይና እና የኢትዮጵያ መንግስታት ከጤናው በተጨማሪ በሌሎችም ዘርፎች አብሮ በመስራት ረዥም ታሪክ እንዳላቸው የጠቀሱት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የሁለቱ ሀገራት የቆየ ወዳጅነትና ትስስር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸዉን እምነት ገልፀው፣ የጤና ቡድኑ በኢትዮጵያ በገኘት ለሚያደርገው የጤና አገልግሎት ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
ቻይና ወደ ኢትዮጵያ የህክምና ቡድን በተለያየ ዙር ስትልክ ሃምሳ ዓመታትን እንዳስቆጠረች የገለፁት ዶ/ር ሶንግ ወንጋግ፣ በቀጣይም በጥሩነሽ ቤጅንግ ሆስፒታል አዲስ ለሚገነባው የትራዉማ ማዕከል የድጋፍ አገልግሎት አሰጣጡ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል፡፡
ላለፈው አንድ ዓመት በጥሩነሽ ቤጅንግ ሆስፒታል የቻይና የጤና ቡድኑ ሰፊ አገልሎት ሲሰጥ እንደነበር የጠቀሱት በጤና ሚኒስቴር የሜዲካል አገልግሎት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኢሉባቦር ቡኖ፣ የጤና ቡድኑ አባላት ላበረከቱት አስተዋፅኦ ከፍተኛ አድናቆት እንዳለቸው ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም ኢትዮጵያ እና ቻይና በጠንካራ ወዳጅነት መንፈስ እና በአጋርነት እንዲሰሩ የማመቻቸቱን ሚና በላቀ አፈፃፀም ለሚወጣዉ የቻይና ኤምባሲ ከፍተኛ አድናቆት እንዳላቸው የገለፁት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ፣ የጤና ቡድኑ አባላት ላበረከቱት አስተዋፅኦ የማረጋገጫ ምስክር ወረቀትም ሰጥተዋል፡፡