የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋፅዖ እውቅና አገኙ 

  • Time to read less than 1 minute
#AHAIC2023

እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግድሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት ላይ አልፎም ሁሉአቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ እንዲሁም ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጥ ሲሆን የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ  ታደሰም ለዜጎች የተሻለ እና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል። 

በዛሬዉ ዕለት በሩዋንዳ ኪጋሊ እየተካሄደ በነበረዉ #AHAIC2023 ላይ ይህ Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተበርክቶላቸዋል።