የፖላንድ ህክምና ቡድን ለሁለተኛ ጊዜ ሲያከናውን የነበረውን የነፆ ህክምና አገልግሎት አጠናቀቀ

  • Time to read less than 1 minute
Medical Team

የፖላንድ ህክምና ቡድን ለሁለተኛ ጊዜ ከየካቲት 17 እስከ 26, 2015 ዓ.ም ድረስ በጥቁር አንበሳ እና በጦር ሀይሎች ስፔሻይዝድ ሆስፒታል ሲያከናውን የነበረውን የነፆ ህክምና አገልግሎት አጠናቀቀ።

ሰላሳ አንድ የበጎ ፍቃደኛ የህክምና ባለሙያዎች ያቀፈው ቡድን የነርቭ፣ የአጥንት፣ የኩላሊት፣ የሽንት ፊኛና የሽንት ቧንቧ የቀዶ ህክምና አገልግሎቶችን የሰጠ ሲሆን ከኢትዮጵያን የህክምና ባለሙያዎች ጋር በተጠቀሱት የስፔሻሊቲ ዘርፎች ላይ የልምድ ልውውጥ አድርጓል።

ከዚህ በተጨማሪ ለህክምና አገልግሎቱ የዋሉ የህክምና መሳሪያዎችንና ግብአቶችን በእርዳታ ከፖንላድ ይዞቸው መምጣቱ ታውቋል።

የጤና ሚኒስተር የህክምና ቡድኑ አባላትና ይህ ዘመቻ የተሳካ እንዲሆን ላገዙ አካላት ምስጋና ያቀርባል።