የኮቪድ 19ን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም የሚያግዝ ሰው ሰራሽ መተንፈሻ መሳሪያ ድጋፍ ርክክብ ተደረገ

  • Time to read less than 1 minute
Delivery

ግምታቸው 30 ሚሊዮን ብር የሚሆን 100 ሰው ሰራሽ መተንፈሻ መሳሪያዎች የኮቪድ 19ን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም የሚያግዝ ሰው ሰራሽ መተንፈሻ መሳሪያ ድጋፍ ለጤና ሚኒስቴር ተደርጓል፡፡

 
ድጋፉን ለጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ  ያስረከቡት የሞደርን ኢ.ቲ.ኤች አውት ሶርስ ፒ.ኤል.ሲ ተወካይ የሆኑት አቶ ታዲዮስ ተፈራ፤ ድጋፉ የተደረገው በኮቪድ የተጠቁ ዜጎችን ለመርዳት ታስቦ መሆኑን ገልጸው ድጋፋቸው የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 
 የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ፣ ድጋፉን ያደረጉትን ድርጅቶች አመስግነው፤ መሳሪያዎቹ በጽኑ ህሙማን ማገገሚያ የሚገኙ ታካሚዎችን ለመርዳት ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርጉ ገልጸው ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

 
በርክክብ ዝግጅቱ ላይ የህክምና መሳሪያዎቹን ድጋፍ ያደረጉ እና እቃዎቹን ወደ ሀገር ቤት በማጓጓዝ ያስረከቡ ድርጅቶች ከጤና ሚኒስቴር የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል፡፡