Announcement

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ

የጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሜዲስን፤ ነርሲንግ፤ ጤና መኮንን፤ አንስቴዥያ፤ ፋርማሲ ፤ሜዲካል ላቦራቶሪ፤ ሚድዋይፈሪ፤ ዴንታል ሜዲስን፤ ሜዲካል ራዲዮሎጂ፤ ኢንቫይሮመንታል ሄልዝ፤ ፔዲያትሪክ ኤንድ ቻይልድ ሄልዝ፤ ሳይካትሪ ነርሲንግ፤ እና ኢመርጀንሲ ኤንድ ክሪቲካል ኬር ነርሲንግ ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ፈተናው ከግንቦት 14- 18/ 2015 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን እየገለፅን :-

  1. የፈተናው አሰጣጥ ሂደት በኮምፒውተር ይሆናል።
  2. የፈተናው መርሃግብር
    • - 14/9/2015 ዓ.ም…………………………………Nursing
    • - 16/9/2015 ዓ.ም…………………………………Pharmacy, Public Health, Anesthesia, Medical Radiology Technology and Environmental Health
    • - 18/9/2015 ዓ.ም………………………………..Medical Laboratory Science, Midwifery, Medicine, Dental Medicine, Pediatric and Child Health Nursing, Psychiatric Nursing and Emergency and Critical Care Nursing
  3.  እያንዳንዱ ተፈታኝ ከሚፈተንበት ቀን አንድ ቀን ቀደም ብሎ ማለትም ግንቦት 13፣15 እና 17/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ በ 3፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ (orientation) መከታተል፤ የቅድመ ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን መስራትና፤ የመፈተኛ ክፍሉን መለየት ይኖርበታል:: በፈተና ገለፃው (orientation) ላይ ያልተገኘ ተመዛኝ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።
  4. በፈተናው ዕለት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ህጋዊ መታወቂያ)፣ የፈተና መስሪያ ግብዓቶች (እስኪሪብቶ ብቻ) ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡
  5. ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች ውጪ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎች እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡
  6. በፈተናው ወቅት ተመዛኞች በሁለቱም ክፍለ ጊዜ (ጠዋት እና ከሰዓት በኋላ) አቴንዳንስ ላይ በአግባቡ መፈረማችሁን ማረጋገጥ ይኖርባችኋዋል፣
  7. ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲመጣ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) QR code የያዘ ወረቀት /ስሊፕ/ print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡