D/r Abiy Ahmed

በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልየታደሱ የህሙማን ማረፊያ ክፍሎች በጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተመርቋል:: dawit.berhanu Mon, 09/09/2019 - 10:34

በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የታደሱ የህሙማን ማረፊያ ክፍሎች እና በ326 ሚሊኒዮን ብር በመንግስት ወጪ የተገነባውና 320 አልጋዎችን የያዘው የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በዛሬው እለት በጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ተመርቋል:: በክረምት በበጎ ፍቃደኝነት አገልግሎት ለጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ዕድሳት የገንዘብ ድጋፍ ላደረጉ ባለሃብቶች እውቅና ተሰጥተዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የታደሱ ክፍሎችንና ታካሚዎችን ተዘዋውሮ ጎብኝተዋል::