ማስታወቂያዎች

         ማስክ ኢትዮጵያ ውድድር


  • የመጀመሪያው የምትሳተፉበት ውድድር የፎቶግራፍ ውድድር ነው፡፡ ፎቶግራፉ፣ የማስክን ጠቀሜታ የሚያስታውስ እስከሆነ ድረስ፣ ጥቁር እና ነጭም፣ ባለ ቀለምም ሊሆን ይችላል፡፡ ፎቶግራፉ፣ ግለሰብ፣ ወይም፣ እንደ ቤተሰብ፣ ጓደኞች የመሳሰሉ ቡድኖች ያሉት ሊሆን ይችላል፡፡ አንድ ግለሰብ ወይም ቡድን፣ በአንድ ፎቶ ብቻ ነው መወዳደር የሚችለው፡፡

 

  • ሁለተኛው ውድድር፣ የቪዲዮ ማስታወቂያው ነው፡፡ የማስክን ጠቀሜታ የሚያስታውስ እስከሆነ ድረስ፣ የቪዲዮ ማስታወቂያው፣ ጥቁር እና ነጭም፣ ባለ ቀለምም፣ ሊሆን ይችላል፡፡ በድምጽ፣ እና በምስል ተቀናብሮ የሚላከው የቪዲዮ ስራ፣ ርዝማኔው፣ ከ30 ሰከንድ መብለጥ አይኖርበትም፡፡

 

  • ሶስተኛው ውድድር፣ የሬዲዮ ማስታወቂያ ሲሆን፣ የማስክን ጠቀሜታ የሚያስገነዝብ፣ ተሰርቶ ያለቀ፣ በሬዲዮ የሚተላለፍ መልእክት ነው፡፡ የሬዲዮ ማስታወቂያው ርዝማኔ፣ ከ 30 ሰከንድ መብለጥ አይኖርበትም፡፡

 

  • አንድ ግለሰብ ወይም ቡድን፣ በአንድ ዘርፍ ብቻ ነው መወዳደር የሚችለው፡፡

 

  • ተወዳዳሪዎች፣ ስራዎቻችሁን ስትልኩ፣ ሙሉ ስማችሁን እና አድራሻችሁን መግለጽ ይኖርባችኋል፡፡

 

  • ተወዳዳሪዎች፣ ስራዎቻችሁን፣ እስከ ነሀሴ 18፣ 2012 ድረስ፣ በጂ ሜይል አድራሻችን moh@moh.gov.et እና maskethiopia@gmail.com እንድትልንኩልን እንጠይቃለን፡፡

 

  • በሶስቱም ዘርፎች አንደኛ አንደኛ የወጡ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች፣ የገንዘብ እና የሰርቲፊኬት ሽልማት ይበረከትላቸዋል

                                               

                                                                መልካም ውድድር! መልካም ሽልማት!

Amharic