የጤና ሚኒስቴር የደም ልገሳ ባህልን ለማሻሻል የተለያዩ ስትራቴጂዎችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስታወቀ

Submitted by dawit.berhanu on Sat, 10/26/2019 - 12:29

ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ በዛሬው እለት የብሄራዊ የደም ባንክ ህንጻ ምርቃት ላይ ባደረጉት ንግግር በሀገር አቀፍ ደረጃ "ህይወት ለህይወት...ደም ሰጥተን ህይወት እናድን" በሚል መሪ ቃል በመላ ሀገሪቱ በአንድ ጀምበር ብቻ አስር ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ መታቀዱን ገልፀዋል፡፡

ሚኒስቴር ዴኤታዋ አያይዘውም የብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ሀገሪቱ ከደረሰችበት የህክምና ደረጃና ፍላጎት እንዲሁም የጤና ተቋማት መስፋፋት ጋር ተያይዞ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋ የመጣውን የደም ፍላጎት ለሟሟላት ይቻለው ዘንድ ደህንነቱና ጥራቱን የጠበቀ ደምና የደም ተዋጽኦ ለማዳረስ ከፍተኛ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡
አዲሱ የደም ባንክ ህንጻ ከአሜሪካ መንግስት በተደረገ ድጋፍ መገንባቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡