የጤናው ዘርፍ የስራ ኃላፊዎች የተሳተፉበት ምክክርና ውይይት

Submitted by dawit.berhanu on Fri, 05/03/2019 - 12:15

ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች ለማረጋገጥ የጤናው ዘርፍ የወረዳ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ ዓይነተኛ ሚና አለው

የተጀመረው አገር አቀፍ የጤናው ዘርፍ የስራ ኃላፊዎች እየተሳተፉበት ያለው ምክክርና ውይይት እንደቀጠለ ነው

በእስካሁኑም  ውይይት፡-

  • በጤናው ዘርፍ የትራንፎርሜሽን አጀንዳዎች ውህደትና ቅንጅት  (Integration and Coalition) (1 በ4፤ 4 ለ1)
  • የወረዳ ትራንስፎርሜሽኑን ከሰባት ሴክተሮች ጋር በቅንጅት ተግባራዊ የሚደረግበትን አሰራር በተመለከተ
  • በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን፣ በጤና ፋይናንስ ስርዓት፣ በመድሃኒትና የህክምና ግብዓት አቅርቦት እንዲሁም  በመሰረታዊ ጤና አገልግሎት አሃድ
  • እና በሌሎች የትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸምን ላይ ግምገማዊ ስልጠናውን ቀጥሏል፡፡

 

በዚህ ውይይት የሚኒስቴር /ቤቱ፣የተጠሪ ተቋማት፣የክልል ጤና ቢሮዎች፣የዞን ጤና መምርያዎችና የወረዳ ጤና /ቤቶች ስራ ኃላፊዎች እየተሳተፎ ሲሆን በባህርዳርና በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በውይይቱ ላይ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ከአመራርነት ጋር የተገናኙ ማነቃቅያ ስልጠናዎችም እየተሰጡ ነው፡፡