የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በኤርትራ ለሁለት ወራት ያህል የህክምና አገልግሎት በመስጠት ወደ ሀገራቸው የተመለሱትን የህክምና ልዑካን ቡድን አነጋገሩ

Submitted by admins on Wed, 01/02/2019 - 12:26

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በኤርትራ ለሁለት ወራት ያህል የህክምና አገልግሎት በመስጠት ወደ ሀገራቸው የተመለሱትን የህክምና ልዑካን ቡድን አነጋገሩ፡፡

በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ሀገራት መካከል በተደረገዉ ስምምነት መሠረት ላለፉት ሁለት ወራት በኤርትራ ቆይታ በማድረግ የህክምና አገልግሎት ለህዝቡ ሲያበረክቱ ለነበሩት 35 ጠቅላላ ሀኪሞች እና አምስት እስፔሻሊስት ሀኪሞች የአቀባበል ሥነ-ሥርአት ላይ የተገኙት የኤፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ሀኪሞቹ ላበረከቱት ሙያዊ አስተዋፅኦ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከሀኪሞቹ ጋር ባደረጉት ውይይት የህክምና ባለሙያዎቹ ወደፊትም በሀገራቸው ወደ ገጠሪቱ ኢትዮጵያ በመሄድ በሙያቸው ህዝቡን እንዲያገለግሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የኢፌድሪ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር አሚር አማን በበኩላቸዉ የሀኪሞቹ በኤርትራ ቆይታ ማድረጋቸው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ለማጠናከር ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው በመግለጽ ህብረተሰባቸውን በትጋት ማገልገል እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡

ወደ ኤርትራ ከሄዱት ሀኪሞች መካከል ዶ/ር ዳዊት ደግአረገ እና ዶ/ር ሥነጥበብ ታደሠ በበኩ ላቸዉ በኤርትራ ህዝብ በኩል የተደረገላቸዉ ሞቅ ያለ አቀባበል በቆይታቸዉም ወቅት ህዝቡ ላሳያቸዉ ፍቅርና እንክብካቤ በልዑካን ቡድን ስም ምስጋናቸዉን ለኤርትራ መንግስትና ህዝብ አቅርበዋል፡፡