ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው መድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያዎች በትግራይ ክልል ለሚገኙ ጤና ተቋማት ተሰራጭተዋል

Submitted by admins on Tue, 12/22/2020 - 20:30

ጤና ሚኒስቴር ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የተለያዩ መድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያዎች  በትግራይ ክልል ለሚገኙ ለተለያዩ ጤና ተቋማት በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በኩል  ያሰራጨ ሲሆን መድኃኒቶቹና የሕክምና መገልገያዎቹ በመቀሌ፣ በአዲግራትና ሽሬ ከተሞች ለሚገኙ ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች  ለእያንዳንዳቸው 3 በአጠቃላይ 9 መድኃኒት የጫኑ ተሸከርከሪዎችን በማጓጓዝ እንዲደርሳቸው ተደርገዋል። 
 
ከተሰራጩ መድኃኒቶች መካከል መሰረታዊ ህይወት አድን መድኃኒቶችን ጨምሮ ለድንገተኛ፣ ለኩላሊት፣ ለደም ግፊት፣ ለስኳር ሕሙማን እንዲሁም ለእናቶችና ህጻናት ጤና አገልግሎት የሚውሉ ይገኙበታል።

ከዚህ ቀደምም ለምዕራብና ደቡባዊ ትግራይ ዞኖች ዳንሻ፣ ሁመራ፣ ራያ፣ አላማጣ እና ሌሎች አካባቢዎች በአማራና አፋር ክልል የሚገኙ የኤጀንሲው 3 ቅርንጫፎች በኩል የሚያስፈልጉ መድኃኒቶች እና የህክምና ቁሳቁሶች ተሰራጭተዋል።