የሃይማኖት አባቶች በኮሮና ቫይረስ ላይ የጥንቃቄ ጥሪ አስተላለፉ

Submitted by admin on Mon, 03/16/2020 - 16:42

የኢትዮጵያ የሀይማኖት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ዛሬ ባደረጉት አስቸኳይ የጋራ መግለጫ ወቅታዊ እና አለም አቀፋዊ ስጋት በሆነው የኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ለመላው ኢትዮጵያውያን የጥንቃቄ ጥሪ አስተላለፉ፡፡

የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ባስተላለፉት መልእክት የኮሮና ቫይረስ በፍጥነት የሚዛመት መሆኑ አሳሳቢ ቢሆንም አስፈላጊውን የንፅህናና የህክምና ክትትል ማድረግ ከተቻለ በቀላሉ በሽታውን መከላከልና መፈውስ ይቻላል ያሉ ሲሆን ቫይረሱ በንክኪ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ መሆኑን ጠቅሰው በሀገራችን ያለው የአኗኗር ዘይቤ ለዚህ አይነቱ በሽታ ምቹ እንደሚሆን ተገንዝበን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል ብለዋል፡፡

አባቶች ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍል መልክት አስተላልፈዋል፡፡ ምዕመናን እንደየዕምነታችው ለፈጣሪ በማደርና በሙሉ ልብ ንስሀ በመግባት ፈጣሪን እንዲለምኑና በየቤተ-እምነት በሚደረገው የአምልኮ ስነ-ስርአት ይሁን በማንኛውም ማህበራዊ ግንኙነት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

የንግዱ ማህበራሰብ፣ የጤና ድርጅቶችና የጤና ባሙያዎች፣ የመገናኛ ብዙሀን ድርጅቶችና የማህበራዊ ሚዲያ መረጃ አሰራጮች እንዲሁም የመንግስት ሀላፊዎች እንዲህ አይነት ክስተት ሲያጋጥም ድርብ ድርብርብ ሀላፊነት እንደሚወድቅባችሁ በመማን ሙያዊ ስነ ምግባራችሁን አክብራችሁ ላፊነታችሁን ከምንጊዜውም በላይ እንዲትወጡ በማለት መክረዋል፡፡

ምዕመናን በዚህ ረገድ ከመንግስትና ከጤና ሚኒስቴር የሚተላለፉ ሙያዊ መልዕክቶችን እንዲተገብሩ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የሃይማኖት አባቶች የሃይማኖት አባቶች የሃይማኖት አባቶች