የእናቶችን ሞት መቀነስ ቤተሰብንና ሀገርን መታደግ ነው

Submitted by dawit.berhanu on Tue, 01/14/2020 - 14:11

የኢፌድሪ ፕሬዝደንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ በመድረኩ ላይ እንደገለፁት የእናት ሞት አንድ ጊዜ ብቻ አይደለም እያደረ የሚቆረቁር ነው፡፡ ለቤተሰብ መፍረስና ለሀገር ዕድገት ማነቆ ከመሆኑ አንፃር የእናቶች ህክምና በተገቢው ሰአትና ቦታ በሰለጠነ የጤና ባለሙያ ቢሰጥ አብዛኛውን ሞት መከላከል ይቻላል ብለዋል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው በቤት ውስጥ ሳይሆን በጤና ተቋም መውለድ እንዲችሉ የመተግበሪያ አቅጣጫዎች ላይ ኃላፊነት በተሞላበትና በቁርጠኝነት መስራት እንደምያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

በእርግዝና ወቅት በወሊድና ድህረ ወሊድ ጊዜ የደም መፍሰስ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት፤ በመላ ሰውነት የተሰራጨ ኢንፌክሽን እና ንፅህናውን ያልጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ አሁንም የእናት ሞት ምክንያቶች ሆነው ቀጥለዋል፡፡

በመድረኩም ላይ የፈዴራልና የክልል አመራሮች እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በጉዳዩ ላይ ለመስራት ተፈራርመዋል፡፡