ሁለተኛው ሀገር አቀፍ የማህበራዊና የባህርይ ለውጥ ተግባቦት (SBCC) ጉባኤ ተጀመረ

Submitted by dawit.berhanu on Mon, 12/09/2019 - 16:24

ሁለተኛው ሀገር አቀፍ የማህበራዊና የባህርይ ለውጥ ተግባቦት ጉባኤ ‹የማህበራዊ እና የባህርይ ለውጥ ተግባቦት ከጤና ባሻገር› በሚል መሪ ቃል ከህዳር 29 እስከ ታህሳስ 1/2012 ዓ/ም እየተካሄደ ነው፡፡

በማህበራዊ እና የባህርይ ለውጥ ተግባቦት (SBCC) በጤናው ዘርፍ የእናቶችና ህፃናት ሞት ቅነሳ እንዲሁም በተላላፊ በሽታዎችን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ውጤቶች ይመዝገቡ እንጂ አሁንም ቢሆን ያልተፈቱ የጤና ችግሮች አሉ ብለዋል የጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን፡፡

ባልተፈቱ የጤና ችግሮች ላይ ለውጥ ለማምጣት በተዋረድ ያሉ የጤና ባለሙያዎች እና ጤና ተቋማት የማህበራዊ እና የባህርይ ለውጥ ተግባቦት ላይ በትኩረት መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡

በጉባኤው ላይ ከ26 በላይ ጥናታዊ ፁሁፎች፤አነቃቂ ንግግሮች እና የልምድ ልውውጥ ይደረግበታል፡፡ በተጨማሪም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከሚከናወኑ ጥናታዊ ምርምሮች እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት በማህበረሰቡ ውስጥ የሚተገበሩ የተግባቦት ስራዎች ጋር የማጣመር የመፈተሸና ለበለጠ ስኬት የማዘጋጀት አቅጣጫ ይቀመጥላቸዋል፡፡