የጤና ሚኒስቴር፣ የተጠሪ ተቋማት እና የክልል ጤና ቢሮዎች መደበኛ ስብሰባ ተጀምሯል

Submitted by dawit.berhanu on Mon, 10/14/2019 - 11:09

የጤና ሚኒስቴር፣ የተጠሪ ተቋማት እና የክልል ጤና ቢሮዎች መደበኛ ስብሰባ ተጀምሯል

የጤና ሚኒስቴር፣ የተጠሪ ተቋማት እና የክልል ጤና ቢሮዎች የሚያካሂዱት መደበኛ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

በስብሰባው የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማንን ጨምሮ ከተጠሪ ተቋማት እና ከክልል ጤና ቢሮዎች የተውጣጡ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።

በስብሰባው የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት የተከለሰ አዋጅን እና በወረዳ ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ትራንስፎርም ያደረጉ ወረዳዎችን በፌደራል፣ በክልል፣ በዞን እና በወረዳ ደረጃ ማፅደቅ እና የተሞክሮ ትምህርት መውሰድ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ውይይት ይደረጋል።

ከዚህ ባለፈም የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ የተከለሰ አዋጅ፣ የ2019 እ.ኤ.አ የጤና እና ስነ-ሕዝብ ዳሰሳ ውጤት እና በተለያዩ ዘርፎች ቅንጅት እየተሰራ ያለው የወረዳ ትራንስፎርሜሽን የስራ ሂደት የስብሰባው ዋነኛ አጀንዳዎች መሆናቸው ተገልጿል።

እንዲሁም በ21ኛው የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባዔ እና በሀገር አቀፍ የደም ልገሳ መርሃ ግብር ዙሪያ ውይይት የሚደረግ መሆኑን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።