የምስራቅ አፍሪካ የካንሰር ህከምና ማዕከል በኢትዮጵያ ሊገነባ ነው::

Submitted by dawit.berhanu on Tue, 09/17/2019 - 11:12

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት /ኢጋድ/ በምስራቅ አፍሪካ ቀጠናው ያሉ 200 ሚሊዮን ሰዎችን ለመርዳት የሚያስችል የካንሰር ህከምና ማዕከል በኢትዮጵያ እንዲገነባ ወሰነ፡፡

ማዕከሉ 450 ሚሊዮን ዶላር በሚሆን ወጪ ይገነባል ተብሏል፡፡

ኢትዮጵያ ለማዕከሉ ግንባታ በአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር በኩል መሬት ማዘጋጀቷን እና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ የፖለቲካ ቁርጠኝነት እንዳላት የጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን ገልፀዋል ፡፡

ለማእከሉ የገቢ ማሰባሰቢያ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡