በ2011 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ የተሰጠውን የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ውጤት

Submitted by dawit.berhanu on Wed, 08/28/2019 - 18:19

የጤና ሚኒስቴር የአገልግሎት ጥራትን ከማሻሻል አንጻር የተለያዩ ስራዎችን እየተገበረ ይገኛል ከነዚህም መካከል አንዱ የሆነው የጤና ባለሙያዎችን ከተመረቁ በኃላ ብቃታቸውን መዝኖ ወደ ስራ እንዲገቡ የሚያስችል ስርአት መዘርጋት ነው ይህንንም ለማከናወን እንዲያስችል ላለፉት አራት(4) አመታት የተለያዩ ዝግጅቶች ሲደረጉ ከቆዩ በኃላ በዚህ አመት ከሀምሌ 1-9 2011 ዓ.ም ለ10,480 የጤና ሙያ ዘርፍ ተመራቂዎች የብቃት ምዘና የተሰጠን ሲሆን ወጤቱንም ነገ ነሐሴ 23 ቀን 2011ዓ.ም ለጤና ባሙያዎችና ለሚመለከታቸው ተቋማት የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

ተማሪዎች ውጤታቸውን በዌብ ሳይት hple.moh.gov.et በመግባት registration number፣ ስም እና የአባት ስም በማስገባት መመልከት ይችላሉ፡፡