“በጎነት በሆስፒታል”

Submitted by dawit.berhanu on Wed, 08/21/2019 - 12:02

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አነሳሽነት የተጀመረው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መሃከል የሆስፒታል የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ይገኝበታል:: “በጎነት በሆስፒታል” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶች እና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ፣ በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ እና በጤና ሚኒስቴር አስተባባሪነት በ13 የመንግስት ሆስፒታሎች ላይ የተጀመረ ነው::
የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዱላሂ በሆስፒታሎች ባደረጉት ጉብኝት እጅግ አስደሳች እና አበረታች አስተያየቶችን ከህመምተኞች፣ ከቤተሰቦቻቸው እና ከሆስፒታል አስተዳደር ተቀብለዋል:: ይህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በአገር አቀፍ ደረጃ አመቱን ሙሉ እንዲቀጥል እየሰራን እንገኛለን ብለዋል::