ስለ ጤና ጥበቃ ሚ/ር

ኢትዮጵያ ከ1990 ጀምሮ የጤና ዘርፍ ልማት መረሀ ግብር ስታስፈጽም ቆይታለች፡፡ የመርሀ ግብሩ የመጀመሪያ ክፍል በ1994 ዓ.ም ሲጠናቀቅ ሁለተኛው ደግሞ በ1997 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡ ሶስተኛው ክፍል ደግሞ ከ1997-2002 ዓ.ም የሚቀጥል ሲሆን በአሁኑ ጊዜ እየተፈፀመ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የህዝቡን ዲሞክራሲ ማስፋፋትና ህዝቡን ማጠናከሩን ይቀጥላል፡፡ የብዙሀኑ መብትና ግዴታ ሙሉ ለሙሉ እውን እንዲሆን ያላማከለ አመራር አስፈላጊ የሆነ ሚና ተጫውቷል፡፡ የጤና ፓሊሲውም ለዲሞክራሲ መቀጠል የሚሰራና ሁሉ ነገር ያልተመቻቸላቸውን የገጠሩን ህዝብ ፍላጐት ለሟሟላት ጠንከር ያለ ትኩረት የሚሰጥ ነው፡፡

አከራካሪ ቢሆንም የጤና ዘርፍ ልማት መርሀ ግብሩን አቀራረጽና አፈፃፀሙን በይበልጥ የመራው ፓሊሲ ያለማከለ አገዛዝን የሚከተለው ነው፡፡ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ስርአቱን ያለማከለ ለማድረግ አስፈላጊ እርምጃዎች ተወሰደው ሀላፊነቱ በፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ በክልል ጤና ቢሮዎችና በወረዳ ጤና ጣቢያዎች መሀል ተከፋፍሏል፡፡

የጤና ዘርፉ የጤና አገልግሎቶች ኤክስቴንሽን መርሀ ግብርን በማስፈፀም አዲስ የሆነ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ መንገድ በቅርቡ ሚኒስቴሩ አስተዋውቆ ነበር፡፡ በዚህ መርሀ ግብር አፈፃፀም ላይም የመጀመሪያ የጤና አገልግሎት ስትራተጂን የተፉጠነ መስፋፋትን አካሄዱ ላይ አስገብቷል፡፡

በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎት አቅራቦቱ የህዝቡን ፍላጐት እንዲያሞላ መንግስት የተቻለውን እያደገ ይገኛል፡፡ ህዝቡን የሚያገለግልና በቅርቡ ጤናቸው የተጠበቀና ደስተኛ እንዲሆኑ ብቁና ውጤታማ የሆነ የጤና አገልግሎት መስጫ ማቋቋም ምኞታችን ነው፡

Amharic