የተሳትፎ ጥሪ ለጤና ባለሙያዎች

Submitted by admins on Tue, 04/30/2019 - 10:34

ቅዳሜ ሚያዝያ 26 ቀን 2011 ዓ.ም ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በሚደረገው ውይይት 3000 የጤና ባለሙያዎች የሚሳተፉ ሲሆን 1000 ተሳታፊዎች በኦን ላይንና በስልክ በፈቃደኝነት እየተመዘገቡ ናቸው፡፡ 1000 ተሳታፊዎች ደግሞ ከክልሎችና ከሁለቱ ከተማ መስተዳድሮች የጤና ተቋማት የተውጣጡ ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ 1000 የሚሆኑት ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ከአጋር ድርጅቶች፣ ከሙያ ማህበራትና ከግል የጤና ተቋማት ናቸው፡፡

ማሳሰቢያ፣
በኦንላይንና በስልክ የተመዘገባችሁ ተሳታፊዎች ዝርዝራችሁ በጤና ሚኒስቴር ድረ-ገጽ እና በፌስ ቡክ ገጽ የወጣ ሲሆን ተሳታፊዎች ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ አርብ ሚያዝያ 25 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3፡00 ሰዓት በጤና ሚኒስቴር በመገኘት የመግቢያ ባጅ መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡ ቅዳሜ ሚያዝያ 26/2011 ዓ.ም ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ላይ የተሰጣችሁን ባጅ እና መታወቂያ በመያዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መሠብሰቢያ አዳራሽ መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡

ከክልል የምትመጡ(ኦንላይን የተመዘገቡትን ጨምሮ) ተሳታፊዎች ከዚህ በታች በተገለፀው የአስተባባሪዎች አድራሻ ሎጂስቲክና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ በቅድሚያ ማነጋገር ይኖርባችኋል፡፡

ሶማሌ ... አብዱልዋሀብ... 0929935800
አማራ... አቶ ታረኩ... 0930416485
ኦሮሚያ... ዘሪሁን... 0933855366
ቤንሻንጉል ጉሙዝ... ወልተጂ... 0960880064
ሃረሪ... በልስቲ ጣሰው... 0913894386
ትግራይ... ጠአመ አርዶም... 0914106840
ጋምቤላ... ፖል ቤል... 0917805068
ድሬደዋ... ዶ/ር ፉአድ ከድር... 0911766383
አዲስ አበባ.. አንተነህ ምትኩ... 0929084181
ደቡብ... ተስፋዬ... 0911053326
አፋር.. ...ዶ/ር ፈረጅ ... 091 066 0853

በኦንላይንና በስልክ የተመዘገባችሁ ተሳታፊዎች ዝርዝር ይህን ሊንክ ተጭነው ማግኝት ይችላሉ፡፡

የተሳታፊዎች ስም ዝርዝር  Download PDF  or Excel