ብዙ ኢትዮጵያዊያኖች መወገድ በሚችሉ ተላላፊ በሽታዎችና የተመጣጠነ ምግብ ባለመመገብ በሚመጡ በሽታዎች ከመስቃየታቸውና ለሞት ከመዳረጋቸውም በላይ የተላላፊ በሽታዎች ስርጭት በጣም ከፍተኛ ስለሆነ ለሱም የተጋለጡ ናቸው፡፡ ለነዚህና አዳዲስ እየመጡ ላሉ በሽታዎች ምላሽ የኢትዮጵያ መንግስት 20 አመት የሚቆይ የጤና ዘርፍ ልማት ኘሮግራም በ1990 ቀርጾ እያስፈፀመ ይገኛል፡፡

ይህ ኘሮግራም በተለያዩ ደረጀዎች ሲሆን አላማ ያደረገውም ሁሉንም ያካተተና እንደ አንድ የሚሰራ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት የሚሰጥና የህዝብ የጤና ተቋማት ላይ ያተኮረ አገልግሎት መስጠት ነው፡፡ ኘሮግራሙ ያተኮረው በተለያዩ ምክንያት የሚመጡ በሽታዎችን መቆጣጠር፣ መግታት፣ ክትባት መስጠትና ማከም ላይ እንዲሁም አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ነው፡፡

ሁሉም የኘሮግራሙ ደረጃዎች ከድህነት ጋር የሚመጡ የጤና ችግሮችን አውጥቶ ለመቅረፍ ስትራቴጂ ሲኖራቸው በሂደቱ ላይ ቀጣይነት ያለው የመሀከል መንፈቅ ግምግማና የመጨረሻ ምዘናና አመታዊ ግምገማ ስብሰባዎችን በማካሄድ አፈፃፀሙ እንዴት እየሄደ እንደሆነ ያያል፡፡