የሚሊኒየሙ የልማት ግቦች ጋር ለመድረስ ዋና ዋና አገልግሎቶችን በሚገባ ማስፋፋትና ህዝቡ እነዚህን አገልግሎቶች መጠቀምና ፈልጐ መሄድ ለመጨመር የማስፈፀሚያ መንገዶችን በመቀየስ በተለይ ደግሞ የገጠሩን ሰውና ድሀውን ከነዚህ ውስጥ ደግሞ ሴቶችና ልጆች ላይ ማተኮር ያስፈልጋል፡፡ ይሄን እውን ለማድረግ ቅድሚያ የተሰጣቸው፡-

  • የባህሪ ለውጥ ለማምጣት መረጃዎችን መስጠትና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎችን መጠቀም፡፡
  • የጤና አገልግሎቶች ኤክስቴንሽን መርሀ ግብር ማስፈፀም፡፡
  • የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና አገልግሎቶችን ማሻሻል፡፡
  • የአጠቃላይ የድንገተኛ ከወሊድ ጋር የተያያዙ የጤና አገልግሎቶችን ማሻሻል ሌሎች ከኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ጋር ብቻ የተያያዙ እንቅስቃሴዎች፣
  • ከኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ጋር አብረው የሚኖሩ ሰዎችን መብት ለመጠበቅ ፍትሃዊነቱን ማስተካከል በተለይ ከቅጥር ጋር በተያያዘ፡፡
  • ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ለሚያመጣው ችግር ለተጋለጡ ሰዎች ሴፍቲ ኔት ማዘጋጀት፡፡
  • የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እንቅስቃሴዎችን ከሌሎች ዘርፎች ጋር አዋህዶ ማስኬድ፡፡