ማስታወቂያዎች ማስታወቂያዎች

የጨረታ ማስታወቂያ
                     የጨረታ ቁጥር፡- ብግጨ/ግኬቲ/SDG/ጤና ኬላ/09-2010
       
የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ህጋዊ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከዚህ ቀጥሎ በሰንጠረዥ የተመለከተዉን ዕቃዎች መግዛት ይፈልጋል፡፡
 

ሎት

 

የዕቃዉ አይነት

ብዛት

የጨረታ ማስከበሪያ

አንድ

ሶስት አይነት ፋርኒቸሮች

6,400

ብር 100,000.00

ሁለት

የዉሃ ታንከር ባለ1000 Litter

1,600

ብር 30,000.00

ሶስት

የተለያዩ የጤና ኬላ ቁሳቁሶች

60,000

ብር 50,000.00

 
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች፤
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ የድጋፍ ደብዳቤ እና የVAT ሰርተፍኬት ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
 
2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለጹት የህጋዊነት ሰነዶች ጨረታዉ ከመከፈቱ አስቀድሞ ከሚመለከታቸዉ የመንግግት አካላት የተገኙ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ ከሚመለከታቸዉ የመንግስት አካላት የተጻፉ የህጋዊነት ማስረጃዎች ተቀባይነት የላቸዉም፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች ላለማጭበርበር ቃል የሚገባበትን ፎርም ሞልተዉና ማህተም አሳርፈዉ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን የማያሟላ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡ 
 
3. ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ የድጋፍ ደብዳቤ ቢያንስ እስከ ጨረታዉ መክፈቻ ዕለት ድረስ የሚያገለግል መሆን የሚኖርበት ሲሆን የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈበትን የድጋፍ ደብዳቤ የሚያቀርብ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
 
4. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ብር ሶስት S„/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሚ/ር መ/ቤቱ ብሎክ A 2ኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው ከግዥ ኬዝ ቲም መውሰድ ይችላሉ፡፡
 
5. በሎት ሶስት የሚወዳደሩ ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር ናሙና ማቅረብ ያለባቸዉ ሲሆን ናሙናዉም ከጨረታዉ መዝጊያ ሰዓት አስቀድሞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች ናሙናዎቻቸዉ ላይ የድርጅታቸዉን ስም በመጻፍ ማህተም ማድረግ አለባቸዉ፡፡ በዚህ ሁኔታ የማይቀርብ ናሙና እንዲሁም ጨረታዉ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ ናሙና ተቀባይነት የለዉም፡፡ ለእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከሎት ሶስት ጨረታ ይሰረዛል፡፡ 
 
6. ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ሰነዶቻቸዉን በተናጥል (ወይም ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ በግዥ ኬዝ ቲም በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ 
 
7. ቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሽያል ሰነድ ለየብቻዉ ታሽጎ መቅረብ ያለበት ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል ፡፡
 
8. ለጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በሰንጠረዥ በተመለከተዉ የገንዘብ መጠን መሠረት በCPO፤ በጥሬ ገንዘብ፤ በሌተር ኦፍ ክሬዲት፤ በባንክ ዋስትና ወይም በመንግስት የግዢ አፈጻጸም መመሪያ ላይ በተፈቀደዉ በማንኛዉም የዋስትና አይነት በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ስም አሰርተው ከቴክኒካል ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ ኢንሹራንስ ቦንድና ቼክ ተቀባይነት የላቸውም፡፡
 
9. ተጫራቾች ያቀረቡት ቴክኒካል ሰነድ ግንቦት 22 ቀን 2010 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በጨረታ መክፈቻ ስነሥርዓት ላይ ለመገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሚኒስቴር መ/ቤቱ ብሎክ A 2ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው በፋይናንስና ግዢ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ 
 
10. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 
11. ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011 551 91 96 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
   አድራሻ፡- ሠንጋ ተራ ጐማ ቁጠባ ፊት ለፊት 
  የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር 
                                                 አዲስ አበባ