ክቡር የኢፊዲሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሸመ በዘንድሮው (2010) በሁለቱ ምክር ቤቶች መክፈቻ ንግግራቸው ላይ ስለጤና ምን ተናገሩ?

 

 

ክቡር የኢፊዲሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሸመ

በዘንድሮው (2010)  በሁለቱ  ምክር ቤቶች መክፈቻ ንግግራቸው ላይ ስለጤና ምን ተናገሩ?

. . .

በ2009 ዓ.ም በጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም በመታገዝ ፍትሃዊ፣ ተደራሽ፣ እንዲሁም ጥራቱን የጠበቀ መሠረታዊ ጤና አገልግሎት ለመስጠት የሠራነው ሥራ ውጤታማ ነበር፡፡ የእናቶችንና የህፃናትን ጤና አገልግሎት እንዲሁም ተላላፊ በሽታዎችን የመከላከልና ቁጥጥር ሥራው የበለጠ ጥራቱ የተጠበቀ እንዲሆን ከምናደርገው እንቅስቃሴ ባሻገር ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የሚሞተው ሰው ቁጥር እጅግ እየጨመረ የመጣ በመሆኑ በ2010 ዓ.ም ተላለፊ ያልሆኑ በሽታዎችን የመከላከሉ ሥራ ህብረተሰባዊ ንቅናቄ እንዲፈጠር የምንሠራ ይሆናል፡፡

 

ከዚሁ በተጓዳኝ ደግሞ ጥራቱ የተጠበቀ የሆስፒታል አገልግሎት መሠጠቱን የማረጋገጥ፣ እንዲሁም ከመድሃኒት አቅርቦት ጋር የተያያዘ አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ትኩረት ይደረጋል፡፡ በተጨማሪም የግሉ ዘርፍ በተለይም በከተሞች አካባቢ በጤና መስክ አገልግሎት በመስጠት የሚኖራቸውን ሚና ይበልጥ ለማጠናከርና ለማስፋት እንዲሁም የሚሰጧቸው የጤና አገልግሎቶች ጥራታቸውን የጠበቁ እና ሁሉንም ወገኖች የሚያረኩ እንዲሆኑ ተገቢው ድጋፍ፣  የክትትልና ቁጥጥር ሥርዓት እንዲዘረጋ ይደረጋል፡፡

ከሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት አኳያ የጤና ኤክስቴንሽን ሥርዓታችን የጀርባ አጥንት የሆኑት ሴቶች በመሆናቸውም ሀገራችን በእናቶችና ህፃናት ሞት መቀነስ በዓለም የተመሠከረለት ውጤት እንድታገኝ አስችሏታል፡፡ በጡትና ማህፀን ካንሠርን ጨምሮ በቤተሰብ ምጣኔ፣ በአመጋገብ ሥርዓትና በተላለፊ በሽታዎች ዙሪያ የተሰጡ ሥልጠናዎችም ውጤታማ መሆን ጀምረዋል፡፡

. . .

ለተከበሩ የሁለቱ ም/ቤቶችም የ2010 ዓ.ም ውጤታማና መልከም የሥራ ዓመት እንዲሆንላችሁ እየተመኘሁ የኢፌዴሪ መንግሥትም የተጀመረውን የህዳሴ ጉዞ እዳር እንዲደርስ አስፈላጊውን ሁሉ የሚያደርግ መሆኑን እገልፃለሁ፡፡

አመሰግናለሁ !!


ዜና ማህደር ዜና ማህደር