የጤና ጥበቃ እና የሴቶችና ህፃናት ሚኒስቴር የእናቶችንና ህፃናት ቀንን በጋራ አከበሩ

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ከበደ ወርቁመጪውን የ2010 አዲስ ዓመት ለመቀበል የሚስችል አገር አቀፍ የአከባበር በዓላት መካከል ነሃሴ 26/2009 ዓ.ም የእናቶችና ህጻናት ቀን ተብሎ በተሰየመው መሰረት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከሴቶችና ህፃናት ሚኒስቴር ጋር በመሆን በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜድካል ኮሌጅ ሆስፒታልና በጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል በዕለቱ አዲስ የተወለዱ ህጻናትን በመጎብኘት እንዲሁም በኮከበ ፀሀይ የህፃናት ማቆያ ቦታና ጥቃት የደረሰባቸውን ሴቶች ተዘዋውረው በመጎብኘትና የተለያዩ የአዲስ ዓመት ስጦታዎችን በመስጠት አከበሩ፡፡

በጉብኝት ስነስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ከበደ ወርቁ ባደረጉት ንግግር መንግስት ለእናቶችና ህፃናት ሁለንተናዊ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ትኩረት በመስጠት አዲስ የተወለዱ ህፃናት ከተወለዱበት ቀን ጀምሮ የእናት ጡት ወተት በመስጠት እንክብካቤ ሊደረግላቸው እንደሚገባ አሳስበው የእናቶችና ህፃናትን የኑሮ ደረጃ ሊቀይር የሚችል ፖሊሲ ማውጣትና ጉዳዩን የሚከታተል አካል በየደረጃው በማቋቋም ቁርጠኝነቱን አሳይቷል ብለዋል፡፡

የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ደሚቱ አምቢሳ በበኩላቸው የእናቶችናንና ህፃናትን ጤና ለመጠበቅ ባለፉት ዓመታት በተደረጉ ያላሰለሱ ጥረቶች አበረታች ውጤቶች የታዩ መሆናቸውን፤ ለአብነትም በጤናው ዘርፍ በማህበረሰብ ደረጃ በሚሰሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ ስራዎች አያሌ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልፀዋል፡፡ 


ዜና ማህደር ዜና ማህደር