የወባ በሽታን ጨርሶ ለማጥፋት የሁሉም ህብረተሰብ ሚና ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ

በሽታው ላለፉት 12 ዓመታት በወረርሽኝ መልክ አልተከሰተም

የዓለም የወባ ቀን በየዓመቱ ሚያዚያ 17 ቀን ይከበራል፡፡ ዘንድሮም በሀገራችን ለ10ኛ ጊዜ  ‹‹ወባን በጋራ ጨርሶ እናስወግድ›› በሚል መሪ ቃል በጋምቤላ Newsብሄራዊ ክልላዊ መንግስት     በጋምቤላ ከተማ ይከበራል፡፡

ሚያዚያ 12 ቀን 2009 ዓ.ም በፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ወባ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የሚያጠቃ በሽታ ከመሆኑም በላይ 75 በመቶ የሚሆነው የሀገራችን አካባቢ ለወባ በሽታ መከሰት ምቹ መሆኑና 60 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ለበሽታው ተጋላጭ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ነገር ግን እስካሁን በተሰሩ ስራዎች የወባ በሽታ ስርጭቱ ከ1.3 በመቶ ወደ 0.5 በመቶ፣ በወባ የሚያዙ ህሙማን ቁጥር በ50 በመቶ እንዲሁም በበሽታው የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርም 60 በመቶ ቀንሷል፤ በተጨማሪም በሽታው ላለፉት 12 ዓመታት በወረርሽኝ መልክ አልተከሰተም ተብሏል፡፡

በቀጣይም ወባን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ብሎም ጨርሶ ለማስወገድ እንዲቻል የተለያዩ ስልቶች ተነድፈው እየተተገበሩ መሆናቸውን በበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት የወባ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ኬዝ ቲም አስተባባሪ ወ/ሮ ሕይወት ሰለሞን ገልፀዋል፡፡


ዜና ማህደር ዜና ማህደር