የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃን በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የሚገኙ የጤና ተቋማትን ጎበኙ

በሃገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደው የጤናው ዘርፍ ድጋፋዊ ጉብኝት በትግራይ ክልል የማጠቃለያ መድረክ ለመገኘት የተገኙት የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ Newsፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃን በትግራይ ምስራቃዊ ዞን የሚገኙ የጤና ተቋማትን ጎበኙ፡፡

የጉብኝቱ ዓላማም በግንባታ ላይ የሚገኙ የጤና ተቋማት የሚታዩ ክፍተቶች እንዲስተካከሉ ለማድረግ፣ የዘገዩ ካሉም ግንባታቸው እንዲፋጠኑና ግንባታቸው በፍጥነት ተጠናቀው ለህዝቡ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግና የጎደሉትንም ለመሙላት ነው፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ ጉብኝት ካደረጉባቸው ጤና ተቋማትም የብዘት ጤና ጣቢያ የሚገነባው የኦፕሬሽን አገልግሎት መስጫ ግንባታና የፋጼ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንባታ ሲሆኑ የአካባቢው ማህበረሰቦችም ክቡር ሚኒስትሩ በስፍራው ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

ክብር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃን የሁለቱን ጤና ተቋማት ግንባታ ተዘዋውረው ከጎበኙ በኋላ በግንባታው ላይ የሚታዩ ክፍተቶች በፍጥነት ተስተካክለው ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ አሳስበዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ በጉብኝት ማጠቃለያቸው ላይ ከማህበረሰቡ ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም መሰረት በቀጣዮቹ 3 ዓመታት በአገር አቀፍ ደረጃ ከሚገነቡት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች መካከል አንዱ ለጋ/አፈሹም ወረዳ ሆኖ እንደሚገነባላቸውና በፌዴራል ደረጃ ሊሟሉ የሚገቡ ነገሮችንም ለማሟላት ቃል የገቡ ሲሆን በጉሎ መከዳ ወረዳ ግንባታው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የፋጼ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልንም ወደ ስራ ማስገባት የሚያስችሉ የህክምና መሳሪያዎችን ለማሟላት ቃል ገብተዋል፡፡


ዜና ማህደር ዜና ማህደር