"እፎይ ተገላገልን" አሉ የሳቦሪ መንደር እናቶች

Newsሳቦሪ በአፋር ክልል በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ የምትገኝ የገጠር መንደር ናት፡፡በዚች መንደር ውስጥ የሳቦሪ ጤና ጣቢያ ይገኛል፡፡በጤና ጣቢያው የመጀመርያ ልጇን በሠላም ተገላግላ እንደ አካባባቢው ባህል በተዘጋጀው የእናቶች ማቆያ ስፋራ ህጻን ልጇን እያጠባች ያገኘናት ወ/ሮ ፋጡማ ኢብራሂም በፊት በመንደሩ የነበረውን የእናቶችን ውጣ ውረድና ስቃይ እንዲህ ስትል ታስታውሰዋላች " ቀደም ሲል በአቅራቢያችን ምንም ዓይነት ጤና ጣቢያም ሆነ አምቡላንስ አልነበረም ፣ የእኔ እናትን ጨምሮ ብዙ ጎረቤቶቼ ልጆቻቸውን የሚወልዱት በልምድ አዋላጆች… በቤት ውስጥ ነበር በዚህም በጣም ይታመማሉ ፣ ብዙ ደም ይፈሳቸዋል ፣ አልፎ አልፎም የሚሞቱ እናቶች እንደነበሩ አስታውሳለሁ፡፡"

… አሁን ላይ ግን አለች ፋጡማ እጇን ወደ ጤና ጣቢያው እየዘረጋች "በመንደራችን የምታዩት የሳቦሪ ጤና ጣቢያ ተገንብቷል፣ የአምቡላንስ አገልግሎትም ይሰጡናል .. እንደዚህ መሆኑ ወደዚህ መጥተን በሠላም እንድንወልድ ረድቶናል፡፡ …ይገርማችኋል !! ጤና ጣቢያውም ከተገነባ በኃላ እዚህ መጥቶ ለመውለድ አንፈልግም ነበር ፣ነውር ይመስለን ነበር፣ …እዛው በቤታችን መውለድና መቆየት ነበር የምንፈልገው….ይህ ልማድ ግን አሁን ላይ የለም… ሁሉም የሳቦሪ እናቶች እንደ እኔ ወደዚህ መጥተን ነው በሠላም የምንወልደው ፣ ከመውለዳችን በፊትና በኃላም እንደቤታችን የምናርፍበት ሁሉም ነገር ያለው …ብንፈልግ ቡና ..ቢሻን ምግብ አብስለን የምንመገብበት አፋር አሪ ተሰርቶልናል፡፡"አፋር አሪ… በሳቦሪ
እናቶችን ከህመማቸው እፎይ ተገላገልን ያሰኘ የአፋር ባህላዊ የእናቶች ማቆያ ስፍራ


ዜና ማህደር ዜና ማህደር