የእናቶችን ሞት መቀነስ ቤተሰብንና ሀገርን መታደግ ነው

Submitted by dawit.berhanu on Tue, 01/14/2020 - 14:11

የኢፌድሪ ፕሬዝደንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ በመድረኩ ላይ እንደገለፁት የእናት ሞት አንድ ጊዜ ብቻ አይደለም እያደረ የሚቆረቁር ነው፡፡ ለቤተሰብ መፍረስና ለሀገር ዕድገት ማነቆ ከመሆኑ አንፃር የእናቶች ህክምና በተገቢው ሰአትና ቦታ በሰለጠነ የጤና ባለሙያ ቢሰጥ አብዛኛውን ሞት መከላከል ይቻላል ብለዋል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው በቤት ውስጥ ሳይሆን በጤና ተቋም መውለድ እንዲችሉ የመተግበሪያ አቅጣጫዎች ላይ ኃላፊነት በተሞላበትና በቁርጠኝነት መስራት እንደምያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

በእርግዝና ወቅት በወሊድና ድህረ ወሊድ ጊዜ የደም መፍሰስ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት፤ በመላ ሰውነት የተሰራጨ ኢንፌክሽን እና ንፅህናውን ያልጠበቀ ጽንስ ማቋረጥ አሁንም የእናት ሞት ምክንያቶች ሆነው ቀጥለዋል፡፡

በመድረኩም ላይ የፈዴራልና የክልል አመራሮች እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በጉዳዩ ላይ ለመስራት ተፈራርመዋል፡፡

ሁለተኛው ሀገር አቀፍ የማህበራዊና የባህርይ ለውጥ ተግባቦት (SBCC) ጉባኤ ተጀመረ

Submitted by dawit.berhanu on Mon, 12/09/2019 - 16:24

ሁለተኛው ሀገር አቀፍ የማህበራዊና የባህርይ ለውጥ ተግባቦት ጉባኤ ‹የማህበራዊ እና የባህርይ ለውጥ ተግባቦት ከጤና ባሻገር› በሚል መሪ ቃል ከህዳር 29 እስከ ታህሳስ 1/2012 ዓ/ም እየተካሄደ ነው፡፡

በማህበራዊ እና የባህርይ ለውጥ ተግባቦት (SBCC) በጤናው ዘርፍ የእናቶችና ህፃናት ሞት ቅነሳ እንዲሁም በተላላፊ በሽታዎችን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ውጤቶች ይመዝገቡ እንጂ አሁንም ቢሆን ያልተፈቱ የጤና ችግሮች አሉ ብለዋል የጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን፡፡

ባልተፈቱ የጤና ችግሮች ላይ ለውጥ ለማምጣት በተዋረድ ያሉ የጤና ባለሙያዎች እና ጤና ተቋማት የማህበራዊ እና የባህርይ ለውጥ ተግባቦት ላይ በትኩረት መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡

የመቀንጨር ችግርን ለመቅረፍ የተያዘውን እቅድ ከግብ ለማድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲረባረቡ ጥሪ ቀረበ

Submitted by dawit.berhanu on Fri, 11/22/2019 - 09:53


የብሔራዊ ስርዓተ ምግብ ፕሮግራም ዓመታዊ የአፈፃፀም ግምገማ መድረክ በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡


ከስርዓተ ምግብ መስተጓጎል ጋር ተያይዞ የሚመጡት እንደ መቀንጨር ያሉ ችግሮች ከቅርብ አመታት በፊት ትኩረት ሳያገኙ በመቆየታቸው አሁን ላይ ርብርብ የሚጠይቁ ጉዳዮች መሆናቸውን በመድረኩ ላይ የተገኙት የባለድርሻ አካላት መስሪያ ቤቶች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች ገልፀዋል፡፡


የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት ከአሁን በፊት በተከተልነው አካሄድ አሁን ላይ ያለንበት ደረጃ ላይ ደርሰናል፤ ለወደፊት ደግሞ የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ያስቀመጥነው ግብ ጋር ለመድረስ የሚያስችል ስትራቴጂና ስልት መከተል ያስፈላጋል ብለው ለዚህ ደግሞ እንደ ግብአት የሚጠቅሙ ከጉባኤው እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ከከዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ከንቲባ ከሆኑት ሙሪየል ቦውሰን እና ልዑካን ቡድናቸው ጋር ተወያዩ

Submitted by dawit.berhanu on Wed, 11/13/2019 - 15:03

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ከከዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ከንቲባ ከሆኑት ሙሪየል ቦውሰን እና ልዑካን ቡድናቸው ጋር ተወያዩ ሲሆን በጤናው ዘርፍ በጋራ ሊሰራባቸውና ትኩረት የሚሹ አንደ የቅድመ ሆስፒታል ህክምና እርዳታ፣ድንገተኛ ህክምና፣ የአእምሮ ጤና፣ ስፔሺያሊቲ ህክምናዎችና ሌሎችንም በሚመለከት ውይይት አድረርገዋል። 

አዲሱ መሠረታዊ የጤና አገልግሎት ፓኬጅ ይፋ ተደረገ

Submitted by dawit.berhanu on Wed, 11/13/2019 - 10:51

በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተዘጋጀው አዲሱ መሠረታዊ የጤና አገልግሎት ፓኬጅ ዛሬ ይፋ ተደረገ፡፡ 


ፓኬጁ አሁን አገሪቱ የደረሰችበትን ወቅታዊ ሁኔታ እና ዕድገት ከግምት በማስገባት እንደገና ከ14 ዓመታት በኋላ የተከለሰ ሲሆን ክለሳው ከአንድ ዓመት በላይ ጊዜ ፈጅቷል፡፡


የጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚር አማን የፓኬጁን ይፋ መሆን አስመልክተው እንደገለፁት ከ14 ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ በ2005 ተዘጋጅቶ የነበረውን ፓኬጅ አዳዲስና ለስራ አስፈላጊ የሆኑ ዘርፎችን በማካተት እንደገና ይፋ ሆኗል፡፡


ኢትዮጵያ የምዕተ ዓመቱን የልማት ግቦች አሳክታ ከዚያም ወዲህ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለመተግበር ፊርማዋን ያኖረች ሀገር መሆኗን ሚኒስትሩ አስታውሰው ጤና ለሁሉም የሚለውን አገር አቀፍ የጤና መርህ ለማሳካትና ለህብረተሰቡ ተገቢውንና ጥራቱን የጠበቀ የጤና አገልግሎት ለማዳረስ ታልሞ ፓኬጁ መዘጋጀቱን አብስረዋል፡፡