ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች ለማረጋገጥ የጤናው ዘርፍ የወረዳ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ ዓይነተኛ ሚና አለው
የተጀመረው አገር አቀፍ የጤናው ዘርፍ የስራ ኃላፊዎች እየተሳተፉበት ያለው ምክክርና ውይይት እንደቀጠለ ነው
በእስካሁኑም ውይይት፡-
- በጤናው ዘርፍ የትራንፎርሜሽን አጀንዳዎች ውህደትና ቅንጅት (Integration and Coalition) (1 በ4፤ 4 ለ1)
- የወረዳ ትራንስፎርሜሽኑን ከሰባት ሴክተሮች ጋር በቅንጅት ተግባራዊ የሚደረግበትን አሰራር በተመለከተ
- በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን፣ በጤና ፋይናንስ ስርዓት፣ በመድሃኒትና የህክምና ግብዓት አቅርቦት እንዲሁም በመሰረታዊ ጤና አገልግሎት አሃድ
- እና በሌሎች የትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸምን ላይ ግምገማዊ ስልጠናውን ቀጥሏል፡፡
በዚህ ውይይት የሚኒስቴር መ/ቤቱ፣የተጠሪ ተቋማት፣የክልል ጤና ቢሮዎች፣የዞን ጤና መምርያዎችና የወረዳ ጤና ጽ/ቤቶች ስራ ኃላፊዎች እየተሳተፎ ሲሆን በባህርዳርና በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በውይይቱ ላይ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ከአመራርነት ጋር የተገናኙ ማነቃቅያ ስልጠናዎችም እየተሰጡ ነው፡፡