ጋዜጣዊ መግለጫ

የ2012 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የጤናው ዘርፍ ክንዋኔዎች ውጤታማ እንደሆኑ ተገለፀ  

           
ህዳር 12/2019
ለመጀመሪያው ሩብ ዓመት በጤናው ዘርፍ በተያዙ ስራዎች አፈፃፀም ዘርፉ ውጤታማ እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር ገለፀ፡፡


 የ2011 ክንዉኑንና የ2012 እቅዱን በዝግጅት ምዕራፍ በጥልቀት ግምገማ ተደርጎ የ2012 እቅድ በየዘርፉና ከክልሎች ጋር የመናበብ ስራ ከተሰራ በኋላ ወደ ትግበራ ተገብተዋል፡፡ በወረዳ ትራንስፎርሜሽን ትግበራ የላቀ አፈፃፀም ያላቸውን ወረዳዎች ለማረጋገጥና እውቅና ለመስጠት ባደረገዉ እንቅስቃሴ ከድሬደዋ በስተቀር በሁሉም ክልሎች እና የከተማ አስተዳደር በ32 ወረዳዎች፣ በ125 የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አሀድና በ689 ቀበሌዎች በመለኪያው መሠረት ተመርጠው ተልክተዋል፡፡


በዚህም መሰረት ከታዩት 32 ወረዳዎች 12ቱ  አፈፃፀማቸው ≥ 85%  እንዲሁም 17ቱ ወረዳዎች≥ 80% አፈፃፀም ሲኖራቸዉ፤ ከታዩት 125 የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ አሃዶች ዉስጥ 78 ከፍተኛ አፈፃፀም ያላቸዉ መሆናቸዉ እንዲሁ ከታዩት 689 ቀበሌዎች ዉስጥ 349 የሞዴል ቀበሌ ደረጃ ላይ መሆናቸዉ መረጋገጡ ታዉቋል፣ የእናቶች ጤናን ለማሻሻል ትልቅ ድርሻ ያለው የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ባለፉት ሁለት ወራት አፈፃፀሙ 67 በመቶ መድረሱንና የቅድመ ወሊድ ክትትልም 65 በመቶ ማስመዝገብ ተችለዋል፡፡

ዕድሜያቸው ከአንድ ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትን ጤና ለማሻሻል የፀረ አምስት ክትባት በሩብ አመቱ ዉስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ማግኘት የሚጠበቅባቸው ህፃናት ሽፋን 93 በመቶ የደረሰ ሲሆን በሰለጠነ ባለሙያ የሚሰጠው የወሊድ አገልግሎትም 58 በመቶ ሽፋን ላይ ደርሷል፡፡


የማህጸን በር ካንሰር መከላከያ የHPV ክትባትን ለ14 ዓመት ልጃገረዶች ለመስጠት ከታቀደዉ ወስጥ 1.1 ሚሊዮን ( 90 በመቶ)  ልጃገረዶችን መክተብ መቻሉም ታዉቋል፡፡ 
ተላላፍና ተላላፊ የልሆኑ በሽታዎችን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንጻር ብዙ ስራዎች የተሰሩ ስሆን፡- ለአብነትም በ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ለ 564,832 ነፍሰጡር እናቶች የኤች.አይ.ቪ ምርመራ ለማድረግ ታቅዶ 443,339 (78 በመቶ) ላይ ማድረስ የተቻለ ሲሆን የኤች.አይ.ቪ በደማቸዉ ዉስጥ የተገኘባቸዉ 3,545  ለሚሆኑት የፀረኤችአይ ቪ ህክምና ተሰጥቷል፡፡ በአጠቃላይ በሩብ አመቱ ውስጥ የኤች.አይ.ቪ ምርመራና ምክር አገልግሎት ለ1,235,560 ሰዎች ተሰጥቶ ከነዚህም ውስጥ 7,790 የሚሆኑት የኤች አይ ቪ ቫይረስ በደማችው መኖሩን ያወቁ ሲሆን ይህም ቫይረሱ የተገኘባቸው ከመቶምጣኔ 0.63 በመቶመሆኑን ያሳያል፡፡  

 

የወባ ትንኝን ለመቆጣጠር እና የወባ በሽታን ለመከላከል በ2012 የበጀት ዓመት አጎበር ለሚተካላቸው ወረዳዎች የሚሆን  የ3,189,617 አጎበር በግዢ በሂደት ላይ እንደሆነና ከ 3.45  ሚሊየን ቤቶችን ለመርጨት የሚያስችል የጸረ-ወባ የኬሚካል ግዢ በሂደት ላይ መሆኑነና ባለፈው የበጀት ዓመት የተገዙትን 8,055 የርጭት መሳሪያዎች ለወረዳዎች እየተሰራጭ ተደርገዋል፡፡ በሰቆጣቃል-ኪዳን በሚገኙ ወረዳዎች 351,838 አጎበር ለማሰራጨት በተያዘው እቅድ መሰረት 351,838  አጎበር ተሰረጭቷል፡፡

 

የትራኮማ የዓይን ቀዶ ህክምናን በተመለከተ በአማራ፣ በደቡብ እና ኦሮሚያ ክልሎች ለሚገኙ 6400 ሰዎች የአይን ቆብ የማስተካከል ህክምና አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡ 14 ሆሰፒታሎች የቀዶ ህክምና አገልግሎትን ተደራሽነት ለማስፋት በሩብ ዓመቱ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውንም መግለጫው አስፍሯል፡፡


በሀገር አቀፍ ደረጃ 77 ሺ 625 ከረጢት ደም ለማሰባሰብ ታቅዶ 67 ሺ 79 ከረጢት ደም በማሰባሰብ የዕቅዱ ከ86 በመቶ በላይ መፈፀሙንና በማዕከል ደረጃ ባለው የብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት 25 ሺ ደም ለማሰባሰብ ታልሞ 32 ሺ 943 ወይም 132 በመቶ ከዕቅዱ በላይ በመሰብሰብ ውጤታማ ስራ መከናወኑም ታውቋል፡፡በሌላ በኩል በአንድ ጀምበር 10ሺ ዩኒት ደም የመሰብሰብ ዘመቻ  ከ14ሺ በላይ መሰብሰብ መቻሉ በአበረታችና ዉጤታማ ስራ የተሰራ ስሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተከታታይ 300 ሺ ቋሚ ደም ለጋሾችን ለመመዝገብ ባተደረገዉ ጥረት ከ30ሺ በላይ ሰወችን በኦንላይን መመዝገብ የተቻለ በቀጠይ ብዙ መስራት የጠበቅብናል፡፡


በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የህይወት አድን እና የመሰረታዊ መድሃኒቶች አቅርቦት ሽፋን 90 በመቶ ማድረስ ተቸለዋል፡፡


በአሁኑ ወቅት በሀገር ደረጃ 20 ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሎች፤ 89 ጠቅላላ ሆስፒታሎች፤190 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች፤ 3894 ጤና ጣቢያዎች እና 18,317 ጤና ኬላዎች በአገልግሎት ላይ መሆናቸዉ ታዉቋል፡፡ በተጨማሪም አንድ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፤3 ጠቅላላ ሆስፒታል፤ 99 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፤ 62 ጤና ጣቢያ እና 499 ጤና ኬላዎች ከክልሎች ጋር በመሆን በግንባታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ 


በሁሉም ክልሎች ግንባታቸው ተጠናቆ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ 500 የገጠር ጤና ጣቢያዎችን የህክምና አገልግሎት ጥራት ለማሻሻል እንዲቻል ከውሀ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት የንፁህ እና ከፀሀይ ኃይል ኤሌክትሪክ ለማቅረብ በታቀደው መሠረት መረጃ የማጥራት ስራው ተጠናቆ ወደ ትግበራ እየተገባ ነው፡፡  


በሁሉም ክልሎች አገልግሎት እየሰጡ ለሚገኙ የ500 ጤና ጣቢያ የሚሰጡ የአገልግሎቶችን ጥራት ለማሻሻል እንዲቻል በመቀናጆ በጀት የኤሌክትሪክ እና የንጹህ ውሀ አቅርቦት ስራዎችን ለማከናወን በታቀደው መሠረት በሁሉም ክልሎች መረጃዎችን የማጥራት ስራው ተጠናቆ፣ የበጀት ድጋፍ ለሚያደርጉ ለጋሽ ድርጅቶች የዝርዝር ፕሮፖዛል ስራው ተጠናቋል፡፡ 
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሙሉ የበጀት ድጋፍ በማድረግ እየተገነቡ ከሚገኙት ዘጠኝ ጤና ጣቢያዎች መካከል የሶስት ጤና ጣቢያዎች ግንባታ የተጠናቀቀ ሲሆን የቀሪ ስድስት ጤና ጣቢያዎች አማካይ ግንባታ አፈጻጸም 81 በመቶ ላይ ደርሷል፡፡ በተመሳሳይ ከግሎባል ፈንድ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እንዲገነቡ እቅድ የተያዘላቸው 14 ክልላዊ ላብራቶሪዎች ግንባታ እስከ መስከረም 30 ቀን 2012 ዓ.ም ያላቸው የግንባታ አፈጻጸም በአማካይ 71 በመቶ ደርሷል፡፡


ከዚህ በተጨማሪም በፌደራል በጀት ድጋፍ እየተገነቡ ከሚገኙት የአዳማ ህክምና ኮሌጅ የተማሪዎች ዶርሚቶሪ፣ የ13 ክልላዊ ላብራቶሪ ግንባታዎችን በመገንባት የጤና ጥራት ስርዓቱን ለማሻሻል በታቀደው መሰረት የሩብ በጀት ዓመት አፈፃፀምን አስመልክቶ የአዳማ የፀረ ወባ ማሰልጠኛ ማዕከል ህንጻ 100 በመቶ፣ የአዳማ ህክምና ኮሌጅ የተማሪዎች ማደሪያ ህንጻ 100 በመቶ እንዲሁም የ13 ክልላዊ ላብራቶሪዎች የግንባታ አፈጻጸም በአማካይ 71 በመቶ የደረሰ ሲሆን በመሬት አቅርቦት ችግር የነበረባቸው የሐረርና አዲስ አበባ ላብራቶሪዎች መፍትሔ አግኝተው ግንባታቸው እየተከናወነ ይገኛል፡፡ 


ሌሎች የ2011 የተጀመሩ አዳዲስ የካፒታል ፕሮጀክቶች እነሱም በአለርት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገነቡትና ለአርምሀንሰን የምርምር ማዕከል የቢሮ እና የምርምር አገልግሎቶት መስጠት የሚችል የባለዘጠኝ ወለሎች ህንጻ (2B+G+6) ግንባታ 25 በመቶ ለማድረስ ታቅደው 23 በመቶ የተከናወነ ሲሆን፣ በሀገር ደረጃ የመጀመሪያ የሆነው የባለ አስራ አንድ ወለሎች (2B+G+8) የትራውማ ህንጻ ግንባታ አፈጻጸም 17 በመቶ ተገንብቷል፡፡


ከመድሃኒትና ምግብ ቁጥጥር ጋር ተያይዞ ለ6 የህፃናት እና ለ25 ተጨማሪ የህፃናት ምግቦች ጥራትና ደህንነት ማረጋገጫ ፍቃድ ተሰጥቷቸዋል፡፡ እንዲሁም የምግብ ተቋማት የውስጥ ጥራት ማረጋገጥ ሥርዓት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ለማድረግ 7 የምግብ ፋብሪካዎች የውስጥ የጥራት ቁጥጥ ርተደርጓል፡፡ ወደ ሀገር ውስጥ በገቡ 354,763.985 ቶን የምግብ ዓይነቶች ላይ አስፈላጊውን ቁጥጥር በማድረግ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ በ698,552 ቶን ገቢ የምግብ ጥሬ ዕቃዎች  ላይ አስፈላጊውን ቁጥጥር በማድረግ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ በ385.158 ቶን ገቢ የህጻናት ወተት ቁጥጥር ተደርገበት መስፈርቱን ያሟላ በመሆኑ ወደ ሀገር መግባት ችሏል፡፡ በ 26,583.045 ቶን ገቢ የምግብ ጭማሪዎች ቁጥጥር ተደርጎባቸው ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ችለዋል፡፡ በ26,583.045 ገቢ የምግብ ጭማሪዎች ቁጥጥር ተደርጎባቸው ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ ችለዋል፡፡ በ46,325.7 ቶን ወደ ውጭ ሀገር የተላኩ ምግቦች ላይ ቁጥጥር  ተደርጎባቸው ወደ ውጭ ሀገር ተልከዋል፡፡


በተለያየ ምክንያ ትአገልግሎት ላይ ሊውሉ የማይችሉ ምግቦች በአግባቡ መወገዳቸውን ለማረጋገጥ በተሰራ ሥራ 826,908.82 ብር የሚያወጣ እና በጉዞ ወቅት የተበላሸ ምግብ (መሽሩም)፣15 ቶን በጉዞ ወቅት የተበላሸ/የነቀዘ ሩዝ፣ 48.9 ቶን የሚመዝን ተበላሹ፣ በጉዞወቅት ጉዳት የደረሰባቸው፣ ገላጭ ጽሁፍችግር ያለባቸው የተለያዩ ብስኩቶች፣ ቸኮሌቶች፣ ጁሶችና ዘይቶች እንዲሁም 0.2231 ቶን የሚመዝን የማንጎ ጁስ በጉዞ ወቅት በመበላሸቱ ምክንያት እንዲሁም ቦታ አመቻችተዉ እንዲወገድላቸው ያመለከቱ ሁሉ ተስተና ግደዋል፡፡ 


በክረምቱ የበጎ አድራጎት ተግባርም በተለይ ክልሎችን ጨምሮ ከ150 ሺ በላይ ሠራተኞችን በማሳተፍ ከ7.6 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን መትከል መቻሉ ተጠቅሷል፡፡ ወጣቶች በበጎ አደራጎት ስራ በጤና ተቋማት ተደራጅቶ ዘረፈ ብዙ አገልግሎት መሰጠት ችሏል፡፡ ዘጠኝ ባለሃብቶችን እና ድርጅቶችን በማስተባበርና ከ47 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚገኙ አስር ዋርዶች ጉድለታቸው ተስተካክሎ ለአገልግሎት በቅተዋል፡፡ 

በዚህ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የካፒታል ኘሮጀክቶች ገንዘብ እጥረት መፈጠር፣ ከግዥ መጓተቶችና በአንዳነድ አከባቢዎች የፀጥታ ችግሮች ለስራ እንቅፋት ከሆኑት መካከል የሚጠቀሱ ናቸዉ፡፡ 
ለአስፈላጊ መረጃ
ደ/ር ተገኔ ረጋሳ የሚኒስቴሩ ሕዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር                      ሞባይል ሰ/ቁ0904048722 ወይም፣
አቶ ዮርዳኖሰ አለባቸዉ የሚኒስቴሩ ሕዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ም/ዳይሬክተር         ሞባይል ሰ/ቁ0922979760 ያነጋግሩ
 

Amharic