ለጤና ባለሙያዎች ለCOVID-19 ወረርሽ ለመከላከል የቀረበ ጥሪ

Submitted by admin on Tue, 03/31/2020 - 17:38

በዓለም ላይ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሀገራችን ውስጥ መከሰቱም ይታዎቃል፡፡ በመንግሥትና በበጎ ፍቃደኛ ሰዎች ወረርሽኙን ለመቆጣጠጠር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ሲሆን ወደፊት የወረርሽኙ ሁኔታ እየከፋ ከመጣ በርካታ የበጎ ፍቃድ ባለሙያዎችን ማሰማራት ስለሚጠይቅ፤

  1. በጤና ሙያ ተመርቃችሁ ወደ ሥራ ያልተሰማራችሁ
  2. መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት የምትሰሩ የጤና ባለሙያዎች
  3. በጡረታና በተለያዩ ምክንያቶች ከሥራ የተገለላችሁ የጤና ባለሙዎች (ለመደበኛ አገልግሎት)
  4. የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን
  5. የጤና ተማሪዎች (በመንግስትና በግል)

ከመጋቢት 24 ቀን 2012 ጀምሮ ከዚህ በታች በተገለፀው የጤና ሚኒስቴር ድረ-ገፅ እንድትመዘገቡ ሀገራዊ ጥሪ
እናቀርባለን፡፡
ጤና ሚኒስቴር

 

የሃይማኖት አባቶች በኮሮና ቫይረስ ላይ የጥንቃቄ ጥሪ አስተላለፉ

Submitted by admin on Mon, 03/16/2020 - 16:42

የኢትዮጵያ የሀይማኖት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ዛሬ ባደረጉት አስቸኳይ የጋራ መግለጫ ወቅታዊ እና አለም አቀፋዊ ስጋት በሆነው የኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ለመላው ኢትዮጵያውያን የጥንቃቄ ጥሪ አስተላለፉ፡፡

የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ባስተላለፉት መልእክት የኮሮና ቫይረስ በፍጥነት የሚዛመት መሆኑ አሳሳቢ ቢሆንም አስፈላጊውን የንፅህናና የህክምና ክትትል ማድረግ ከተቻለ በቀላሉ በሽታውን መከላከልና መፈውስ ይቻላል ያሉ ሲሆን ቫይረሱ በንክኪ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ መሆኑን ጠቅሰው በሀገራችን ያለው የአኗኗር ዘይቤ ለዚህ አይነቱ በሽታ ምቹ እንደሚሆን ተገንዝበን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል ብለዋል፡፡

አባቶች ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍል መልክት አስተላልፈዋል፡፡ ምዕመናን እንደየዕምነታችው ለፈጣሪ በማደርና በሙሉ ልብ ንስሀ በመግባት ፈጣሪን እንዲለምኑና በየቤተ-እምነት በሚደረገው የአምልኮ ስነ-ስርአት ይሁን በማንኛውም ማህበራዊ ግንኙነት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

ETHIOPIA CONFIRMED THE FIRST CASE OF COVID-19

Submitted by dawit.berhanu on Fri, 03/13/2020 - 15:13

Ethiopian Public Health Institute has confirmed the positive test in Ethiopia for COVID-19. The person found positive is a 48-year-old Japanese citizen who came to Ethiopia on March four, 2020 from Burkina Faso. Ethiopia has put in place a disease surveillance program since the outbreak of COVID-19 in China, and it has now identified the first positive case in the country. The patient is currently isolated at our facility. He is undergoing medical follow up and is in a stable condition. Those who have been in contact with this person are being traced and quarantined. 

በአገራችን፣ የኮሮና ቫይረስ ያለበት የመጀመሪያው ሰው ተገኝቷል

Submitted by dawit.berhanu on Fri, 03/13/2020 - 15:10

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ በቫይረሱ የተያዘ ግለሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱን አረጋገጠ፡፡ ግለሰቡ፣ የ48 አመት የጃፓን ዜጋ ሲሆን፣ የካቲት 25/ 2012 ዓ/ም ከ ቡርኪና ፋሶ ወደ አዲስ አበባ መምጣቱ ታውቋል፡፡ ኢትዮጵያ፣ በሽታው ከተከሰተ ጊዜ  ጀምሮ በተዘረጋው የተጠናከረ የበሽታዎች ቅኝት ስራ፣ የመጀመሪያውን ታማሚ ለመለየት ችላለች፡፡ ከበሽተኛው ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው ግለሰቦችም የመለየትና ክትትል የማድረግ ስራ ተጀምሯል፡፡ ታማሚው፣ አስቀድሞ በተዘጋጀው  የለይቶ ማከሚያ፣ ተገቢው የሕክምና ክትትል እየተደረገለት ሲሆን፣ እስካሁን ባለው ሁኔታ የከፋ የጤና እክል አልገጠመውም፡፡ 

ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ

Submitted by dawit.berhanu on Thu, 03/12/2020 - 15:30

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 14ኛ መደበኛ ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የቀረበለትን የተለያዩ የሚኒስትሮች ሹመት ተቀብሎ አጽድቋል። ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮች እና ሰራተኞች መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው እንመኛለን፡፡