በአገራችን የኮሮና ቫይረስ መገኘቱ ሪፖረት ከተደረገ ጀምሮ (መጋቢት 4 2012) የኮሮና ቫይረስ /ኮቪድ 19/ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማ እንደነበሩ ተገለፀ፡፡

Submitted by admin on Tue, 06/23/2020 - 16:41

በአገራችን የኮሮና ቫይረስ መገኘቱ ሪፖረት ከተደረገ ጀምሮ (መጋቢት 4 2012) የኮሮና ቫይረስ /ኮቪድ 19/ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማ እንደነበሩ ተገለፀ፡፡
 

በጤና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግጫ እንደገለጹት ኮሮና ቫይረስን በአገር አቀፍ ደረጃ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በፌደራል፣ በየክልሎችና በየተቋማቱ ያሉትን አደረጃጀቶችና ተቋማት ዓቅም ለማጠናከርና ለመደገፍ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ መንግስት የችግሩን ጥልቀት አስቀድሞ በመገንዘብ የተለያዩ አደረጃጀቶችን ሚኒስቴር መስርያ ቤቶችን ጭምር በማደራጀት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ በሙሉ ዓቅሙ እየሰራ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

መደበኛ የጤና አገልግሎቶች በነበሩበት ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገለፀ

Submitted by admin on Fri, 04/24/2020 - 12:01

የኮቪድ-19ን ወረርሽኝን ምክንያት በማድረግ አንድ አንድ የጤና ተቋማት አገልግሎት ማቆማቸው በመደበኛው የጤና አገልግሎቶች ላይ መስተጓጎል እንዳስከተለ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ለኮሮና ቫይረስ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ከተለዩት የጤና ተቋማት ዉጪ ሁሉም የጤና ተቋማት እንደተለመደው መደበኛዉን የጤና አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ዶ/ር ደረጀ አያይዘውም በተለይ በእናቶች እና ህፃናት ጤና አገልግሎት፣ ተላላፊ እና ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ህክምና ላይ መደበኛ አገልግሎት መስጠታቸውን የሚከታተል ግብረ ሀይል ከፌደራል እስከ ወረዳ ድረስ ተቋቁሞ ወደ ስራ ተገብቷል ብለዋል፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት የህክምና ተቋሞቻቸውን የዘጉ የግል ጤና ተቋማት እንዳሉም የተደረሰበት ሲሆን ተግባራቸው ትክክል እንዳልሆነ እና በፍጥነት ሁሉም ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ ይደረጋል።

የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ላይ ለመሰማራት ለተመዘገባችው ጤና ባለሙያዎች በመሉ!

Submitted by admin on Sun, 04/05/2020 - 11:18

የCOVID-19 ወረርሺኝን ለመግታት መጋቢት 24/2012 ዓ.ም በጤና ሚኒስቴር ድህረ- ገጽ ላይ በወጣው
ማስታወቂያ የተመዘገባችሁ ባለሙያዎችን ወደ ስራ ለማሰማራት በቅድሚያ ከስራው ጋር የተያያዘ እውቀት፣ ክህሎት
ብሎም አመለካከት ለማሳደግ ከዚህ በታች በተመለከተው መሰረት በonline course እንድትወሰዱ እያሳሰብን
ስልጠናውን እንደጨረሳችሁ ማጠናቀቃችሁን የሚገልጽ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ከሲስተሙ ፕሪንት በማድረግ
እንድትወስዱ በትህትና እንጠይቃለን፡፡

ወደ covid19-IPC Online course ለመግባት በሚከተለው አድራሻ (ሊንክ) ይጠቀሙ

ለጤና ባለሙያዎች ለCOVID-19 ወረርሽ ለመከላከል የቀረበ ጥሪ

Submitted by admin on Tue, 03/31/2020 - 17:38

በዓለም ላይ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሀገራችን ውስጥ መከሰቱም ይታዎቃል፡፡ በመንግሥትና በበጎ ፍቃደኛ ሰዎች ወረርሽኙን ለመቆጣጠጠር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ሲሆን ወደፊት የወረርሽኙ ሁኔታ እየከፋ ከመጣ በርካታ የበጎ ፍቃድ ባለሙያዎችን ማሰማራት ስለሚጠይቅ፤

  1. በጤና ሙያ ተመርቃችሁ ወደ ሥራ ያልተሰማራችሁ
  2. መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት የምትሰሩ የጤና ባለሙያዎች
  3. በጡረታና በተለያዩ ምክንያቶች ከሥራ የተገለላችሁ የጤና ባለሙዎች (ለመደበኛ አገልግሎት)
  4. የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን
  5. የጤና ተማሪዎች (በመንግስትና በግል)

ከመጋቢት 24 ቀን 2012 ጀምሮ ከዚህ በታች በተገለፀው የጤና ሚኒስቴር ድረ-ገፅ እንድትመዘገቡ ሀገራዊ ጥሪ
እናቀርባለን፡፡
ጤና ሚኒስቴር

 

የሃይማኖት አባቶች በኮሮና ቫይረስ ላይ የጥንቃቄ ጥሪ አስተላለፉ

Submitted by admin on Mon, 03/16/2020 - 16:42

የኢትዮጵያ የሀይማኖት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ዛሬ ባደረጉት አስቸኳይ የጋራ መግለጫ ወቅታዊ እና አለም አቀፋዊ ስጋት በሆነው የኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ ለመላው ኢትዮጵያውያን የጥንቃቄ ጥሪ አስተላለፉ፡፡

የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ባስተላለፉት መልእክት የኮሮና ቫይረስ በፍጥነት የሚዛመት መሆኑ አሳሳቢ ቢሆንም አስፈላጊውን የንፅህናና የህክምና ክትትል ማድረግ ከተቻለ በቀላሉ በሽታውን መከላከልና መፈውስ ይቻላል ያሉ ሲሆን ቫይረሱ በንክኪ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ መሆኑን ጠቅሰው በሀገራችን ያለው የአኗኗር ዘይቤ ለዚህ አይነቱ በሽታ ምቹ እንደሚሆን ተገንዝበን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል ብለዋል፡፡

አባቶች ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍል መልክት አስተላልፈዋል፡፡ ምዕመናን እንደየዕምነታችው ለፈጣሪ በማደርና በሙሉ ልብ ንስሀ በመግባት ፈጣሪን እንዲለምኑና በየቤተ-እምነት በሚደረገው የአምልኮ ስነ-ስርአት ይሁን በማንኛውም ማህበራዊ ግንኙነት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡