የአጋርነት እና ትብብር ዳይሬክቶሬት

ራዕይ

በኢትዮጵያ ቀልጣፋ ፣ ዘላቂ እና ፍትሃዊ የጤና ፋይናንስ ለማየት።

 

ተልዕኮ

የጤና ሴክተር ትራንስፎርሜሽን ዕቅድን ለማሳካት ሀብቶችን መለየት ፣ማሰባሰብ፣ ማንቀሳቀስ ፣ መመደብና በአግባቡ መጠቀምን ለማረጋገጥ ከሚኒስቴሩ ሌሎች ዳይሬክቶሬቶች፣መንግሥት ድርጅቶች ፣ የግሉ ዘርፍና የልማት አጋሮች ጋር ቅንጅትንና አጋርነትን  መመስረት።

 

አጠቃላይ ሚናዎች እና ኃላፊነቶች

• ዳይሬክቶሬቱ የጤና አገልግሎት ፋይናንስ ስትራቴጂን የመተግበር እና የመምራት ኃላፊነት አለበት።

• የአዳዲስና የነባር ጣልቃ ገብነቶች ወጪ ቆጣቢነትን የመገምገምና የማረጋገጥ ሚና አለው።

• እንዲሁም የሀብት ካርታ፣ አሰላለፍ ፣ ምደባና የፋይናንስ ሀብቶችን ቀልጣፋ አጠቃቀም ያረጋግጣል።

• የጤናውን ዘርፍ እርዳታዎች ይከታተላል ፣ ያስተዳድራል።

• በጤና ኢኮኖሚና ፋይናንስ ትንተና ማስረጃን ያመነጫል።

 

5 የጉዳይ ቡድኖች አሉት

 

1) የሀብት ማሰባሰብ ቡድን

2) የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ማስተባበሪያ ቡድን

3) የጤና ኢኮኖሚ-የፋይናንስ ትንተና ቡድን

4) የግራንት አስተዳደር ቡድን

5) የአጋርነት ማስተባበር ቡድን

 

ቁልፍ ስትራቴጂያዊ ተነሳሽነት

1. የሀብት ማሰባሰብ ቡድን

• የሀብት ማሰባሰብ ቡድኑ ከውጭ (ልማት እና ትግበራ አጋሮች) እና የአገር ውስጥ ምንጮች (ግምጃ ቤት ፣ ኢንሹራንስ ፣ የፈጠራ አቀራረብ) ሃብትን የማሰባሰብ ተነሳሽነት አለው።

• ቡድኑ በየአመቱ የሀብት ካርታ ፣ የሀብት ምደባ ፣ አሰላለፍ እና ክፍተት ትንተና ያካሂዳል።

• በጤና አገልግሎት ፋይናንስ ማሻሻያዎች አፈፃፀም ላይ ተከታትሎ የቴክኒክ ድጋፍ ያደርጋል።

• የእርዳታ ስምምነትን (የቅድሚያ ሽልማት የእርዳታ አስተዳደር) ለመፈረም የለጋሽ ዕርዳታ ፕሮፖዛል አመሰራረት፣ ግምገማ እና ማመቻቸት ላይ ይሠራል

 

 2. የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ማስተባበሪያ ቡድን

• የCSO ቡድን በሀገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ የሚሆኑ በሲቪል ማህበራት ድርጅቶች የቀረቡ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ያስተባብራል፣ ግምገማና ድጋፍ ያካሂዳል።

• የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ፕሮጀክቶች ትግበራ ክትትልና ግምገማ ያካሂዳል።

• ቡድኑ ከተግባራዊ አጋሮችና ከክልል ጤና ቢሮ ተጓዳኝ ክፍሎች ጋር የአጋርነት ፎረምን የማደራጀትና የማስተላለፍ ኃላፊነት አለበት

 

3. የአጋርነት ማስተባበሪያ ቡድን

•የአጋርነት ማስተባበሪያ ቡድኑ በጤናው ዘርፍ ላይ ከተለያዩ ሀገሮች ጋር የሁለትዮሽ ስምምነቶችን መፈረምና መተግበርን የማስተባበር ኃላፊነት አለበት።

• ቡድኑ የአገሪቱን የጤና ዘርፍ ለመደገፍ ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ ጋር ተባብሮ ይሠራል።

• ቡድኑ የሕጋዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀትና የአዋጭነት ሥራን ማካሄድ እንዲሁም በመንግሥት-ከግል አጋርነት አሠራር ስር ያሉ ፕሮጀክቶችን ትግበራ ያነሳሳል።

 

4. የጤና ኢኮኖሚ-የገንዘብ ትንተና

የፋይናንስና ኢኮኖሚያዊ ማስረጃዎችን ማመንጨት

• ቡድኑ የተለያዩ የጤና ጣልቃ ገብነቶችን የአሠራር ብቃትና ውጤታማነት የመገምገም ኃላፊነት አለበት

• የፋይናንስ ፍትሃዊነትንና የጤና ሂሳብ ጥናት (የህዝብን የጤና ወጪ) ግምገማ ያካሂዳል

• እንዲሁም የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ግምገማ/ጥናት ያካሂዳል።

 

5.የግራንት አስተዳደር

• የግራንት አስተዳደር ቡድኑ እያንዳንዱን ግራንት በስምምነት ሰነዳቸው ላይ የመመዝገብና የመቆጣጠር ኃላፊነት አለበት

• ከተለያዩ ዕርዳታዎችን ሊጠበቁ የሚችሉ አደጋዎችን በመለየት ይሠራል እና በዚሁ መሠረት ያስተዳድራል።

• ቡድኑ ለእያንዳንዱ የእርዳታ ስምምነት ዝርዝር የአፈጻጸም ዕቅድ የማዘጋጀት ፣ የእርዳታውን ልዩ አቅርቦቶችን የመከታተል እና በየደረጃው (ዳይሬክቶሬቶች ፣ ኤጀንሲዎች እና RHBs) የሚገኙ የተለያዩ ክፍተቶችን የማስተካከያ እርምጃ የመውሰድ ኃላፊነት አለበት።