የሰው ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት

Human resource development

ዓላማ

የሰው ሃብት ልማት እና አስተዳደር ዓላማ በሙያዊ ስነምግባር የሚመሩ የተለያዩ ምድቦች ውስጥ የሚሰሩ ብቁ የጤና ሠራተኞችን ማሠልጠንና ማቅረብ ነው። እንዲሁም አዲስ የሰው ሁብት ልማት ስርዓት መንደፍ እና የማቆያ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት ዓላማ አለው። ቀልጣፋ የጤና አገልግሎቶችን ለማድረስ በቂ ችሎታና ተነሳሽነት ያላቸው እና በደንብ የተደገፉ የጤና ባለሙያዎች መኖር አስፈላጊ ነው።

 

የክፍሉ ዋና ቡድኖች

  • የሰው ሀብት ልማት ቡድን
  • የሰራተኞች አስተዳደር ቡድን

የክፍሉ ዋና ተግባራት

  • ለአዳዲስ የጤና ተቋማት በበቂ ቁጥር የሰለጠነ የሰው ኃይል ማቅረብ
  • በተለያዩ ደረጃዎች እየሠራ ያለውን ነባር የጤና የሰው ኃይል አቅም ማሻሻል
  • ቀጣይ ትምህርትን እና በአገልግሎት ላይ ስልጠናን ማስጀመር እና ማጠናከር
  • የአንዳንድ የጤና ሰራተኞች ምድቦችን ሥርዓተ ትምህርት መገምገም እና ማሻሻል
  • የሰራተኞችን ምድቦች ምክንያታዊ ማድረግ