ራዕይ፣ተልዕኮ ስልጣንና ተግባራት

ራዕይ

ጤነኛ አምራችና ብቁ ዜጐች እንዲኖሩ ማድረግ

ተልዕኮ

በደንብ የተዋሀደ ፈጣንና አጥጋቢ የሆነ የጤና አገልግሎት ብቁ ከሆነ አስተዳደር፣ መቆጣጠሪያ መንገድና እገዛ ጋር መስጠት፡፡

ስትራቴጂአዊ አላማ

  • በእርግዝናና በወሊድ ጊዜ የሚከሰት የእናቶችን ሞት መቀነስ
  • የህፃናትን ሞት መቀነስ
  • የኤች.አይ.ቪ/ኤድስን፣ ሳንባ ነቀርሳን፣የወባ በሽታንና ሌሎች በሽታዎችን መቆጣጠርና ስርጭቱን መግታት፡፡

የሚኒስቴሩ ስልጣንና ተግባራት

  1. የጤና አገልግሎቶች እንዲስፉፉ ማድረግ፣
  2. ሪፈራል ሆስፒታሎች እንዲሁም የጥናትና ምርምር ተቋማትን ማቋቋምና ማስተዳደር፡፡
  3. በጤና አገልግሎቶች መጠበቅ ያለበት ደረጃ ማውጣት፤ ይህ የሚሆነው ስልጣኑ የተሰጣቸው ሌላ አካላት ከሌሉ ብቻ ነው፡፡
  4. በተለያዩ ደረጃ ላይ ያሉ የህብረተሰብ ጤና አገልግሎት ሰጪ ባለሙያዎችን ብቁነት ማረጋገጥና ብቁነታቸውን ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት መስጠት፡፡
  5. ባህላዊ መድሀኒቶች ላይ ጥናቶች እንዲካሄዱ ማድረግና ይሄም እንዲሆን የጥናትና ምርምር ተቋማትን ማደራጀት፡፡
  6. ተላላፊ በሽታዎችን ስርጭት ለመግታትና ለማቆም አመቺ መንገዶችን መቀየስና አፈፃፀማቸውን መከታተል፡፡
  7. የማህበረሰቡን ጤና ለመጠበቅ የታመሙትን ሰዎች ካልታመሙት በማራቅ አስፈላጊ እርመጃ መውሰድ፡፡
  8. የተለያዩ ምግቦች ያላቸውን የምግብ ይዘት ለማወቅ ጥናቶች ማካሄድ፡፡