ራዕይ
ጤነኛ አምራችና ብቁ ዜጐች እንዲኖሩ ማድረግ
ተልዕኮ
በደንብ የተዋሀደ ፈጣንና አጥጋቢ የሆነ የጤና አገልግሎት ብቁ ከሆነ አስተዳደር፣ መቆጣጠሪያ መንገድና እገዛ ጋር መስጠት፡፡
ስትራቴጂአዊ አላማ
የሚኒስቴሩ ስልጣንና ተግባራት
-
የጤና አገልግሎቶች እንዲስፉፉ ማድረግ፣
-
ሪፈራል ሆስፒታሎች እንዲሁም የጥናትና ምርምር ተቋማትን ማቋቋምና ማስተዳደር፡፡
-
በጤና አገልግሎቶች መጠበቅ ያለበት ደረጃ ማውጣት፤ ይህ የሚሆነው ስልጣኑ የተሰጣቸው ሌላ አካላት ከሌሉ ብቻ ነው፡፡
-
በተለያዩ ደረጃ ላይ ያሉ የህብረተሰብ ጤና አገልግሎት ሰጪ ባለሙያዎችን ብቁነት ማረጋገጥና ብቁነታቸውን ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት መስጠት፡፡
-
ባህላዊ መድሀኒቶች ላይ ጥናቶች እንዲካሄዱ ማድረግና ይሄም እንዲሆን የጥናትና ምርምር ተቋማትን ማደራጀት፡፡
-
ተላላፊ በሽታዎችን ስርጭት ለመግታትና ለማቆም አመቺ መንገዶችን መቀየስና አፈፃፀማቸውን መከታተል፡፡
-
የማህበረሰቡን ጤና ለመጠበቅ የታመሙትን ሰዎች ካልታመሙት በማራቅ አስፈላጊ እርመጃ መውሰድ፡፡
-
የተለያዩ ምግቦች ያላቸውን የምግብ ይዘት ለማወቅ ጥናቶች ማካሄድ፡፡